إعدادات العرض
እነርሱን ያገኛቸው አምሳያ እንዳያገኛችሁ ያሰጋልና እያለቀሳችሁ ካልሆነ በቀር እነዚያ ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መኖሪያ እንዳትገቡ።
እነርሱን ያገኛቸው አምሳያ እንዳያገኛችሁ ያሰጋልና እያለቀሳችሁ ካልሆነ በቀር እነዚያ ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መኖሪያ እንዳትገቡ።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር በሒጅር በኩል አለፍን። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለኛ እንዲህ አሉን: "እነርሱን ያገኛቸው አምሳያ እንዳያገኛችሁ ያሰጋልና እያለቀሳችሁ ካልሆነ በቀር እነዚያ ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መኖሪያ እንዳትገቡ።" ከዚያም ግመላቸውን አንቀሳቀሱና አልፈዋት እስኪሄድ ድረስ በፍጥነት ተጓዙ።»
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili English অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በሠሙዶች መኖሪያ በኩል ሲያልፉ ወደዚህ መንደር የሚገባ ሰው እነርሱ ላይ የደረሰውን በማስተንተን እያለቀሰ ካልሆነ በቀር ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መንደር ከመግባት ወይም ከመምጣት ከለከሉ። ይህም እነርሱን እንዳገኛቸው አይነት ቅጣት እንዳያገኘው ስለሚያሰጋ ነው። ቀጥለው እንስሳቸውን በጩኸት አስነስተው አልፈው እስኪሄዱ ድረስ ፈጥነው ተጓዙ።فوائد الحديث
አላህ ያጠፋቸውን ሰዎች ሁኔታ ማስተንተን እንደሚገባ፤ እነርሱ የወደቁበትን ወንጀል ከመፈፀምም መጠንቀቅ እንደሚገባ፤ ተአምራቶችን ከማስተንተን መዘናጋትን መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
ዘወትር ማልቀስ ስለማይችልና በዚህ ሁኔታ ካልሆነ በቀር ቦታው ላይ መቆየትም ስለተከለከለ የተቀጡ ሰዎች መንደር ላይ ከነርሱ በኋላ ማንም አይኖርበትምም ሀገር ተደርጋም አትያዝም።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በበዳዮች መንደርና በተቀጡ አካባቢዎች በሚታለፍ ጊዜ አላህን መፍራት እንደሚገባ ያነሳሳል። የዝሆኑ ባለቤቶች የጠፉበት በሆነው በዋዲ ሙሐሲር በኩል የሚያልፍም ልክ እንደዚሁ መፍጠን ይገባዋል። በእንደዚህ አይነት አካባቢዎች የሚያልፍ ሰው አላህን ማሰብ፣ መፍራት፣ ማልቀስ፣ ከነርሱና ከሞቱበት ስፍራ ትምህርት መውሰድ፣ ከዚህም አይነት ቅጣት የአላህን ጥበቃ መጠየቅ ይገባዋል።"
ክልከላውና ማስጠንቀቂያው የሠሙድ ህዝቦችና ሌሎችንም እንደነሱ ያሉ ቅጣት የወረደባቸውን አካባቢዎች ያጠቃልላል።
እነዚህን ስፍራዎችና መሬቶች ለመዝናኛነት፣ ለመደሰቻነትና ለመሳሰሉት አላማዎች መያዝ መከልከሉን እንረዳለን።
التصنيفات
የጉዞ ህግጋትና ስነ-ስርዓት