በሙሐመድ ሚስቶች ዙሪያ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታ አሰምተዋል። እነዚህ ሚስቶቻቸውን የሚመቱ ባሎች ምርጦች አይደሉም።

በሙሐመድ ሚስቶች ዙሪያ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታ አሰምተዋል። እነዚህ ሚስቶቻቸውን የሚመቱ ባሎች ምርጦች አይደሉም።

ከኢያስ ቢን ዐብደላህ ቢን አቢ ዙባብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "የአላህን ሴት ባሮች አትምቱ!" ዑመርም ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት እንዲህ አሏቸው: "ሴቶች በባሎቻቸው ላይ እያመፁ ነው።" የዛኔም እንዲመቷቸው ፈቀዱ። የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶች ዘንድ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታቸውን አሰሙ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "በሙሐመድ ሚስቶች ዙሪያ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታ አሰምተዋል። እነዚህ ሚስቶቻቸውን የሚመቱ ባሎች ምርጦች አይደሉም።"»

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶችን ከመምታት ከለከሉ። የአማኞች አዛዥ ዑመር ቢን አልኸጧብም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሴቶች ባሎቻቸውን ተዳፈሩ። ስነምግባራቸውም ተበላሸ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የባልን ሐቅ አለመወጣት እምቢተኝነትን ማሳየት፣ ባልን ማመፅና የመሳሰሉት ምክንያቶች ከተከሰቱ የማያቆስል ምት እንዲመቷቸው ፈቀዱ። ከዛም በኋላ ባሎቻቸው ይህንን ፍቃድ በመጥፎ መንገድ በመጠቀም የሚያቆስል ምት የመቷቸው ሚስቶች የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶች ዘንድ ቅሬታ ሊያሰሙ መጡ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: ከናንተ ምርጦቹ እነዚያ ሚስቶቻቸውን የሚያቆስል ምት የሚማቱት ወንዶች አይደሉም።

فوائد الحديث

ሴቶችን በመልካም መስተጋብር መኗኗር ያለው ደረጃ መገለፁ። ሴቶችን ከመምታት ይልቅ መታገስና ከነርሱ የሚከሰቱን ጥፋቶች ባላየ ማለፍ በላጭ ነው።

አላህ ዐዘ ወጀል ምትን ለአመፃቸው የመጨረሻው መፍትሄ ነው ያደረገው። አላህ እንዲህ ብሏል: {እነዚያንም ማመፃቸውን የምትፈሩትን ገስፁዋቸው። በመኝታዎችም ተለዩዋቸው። (ሳካ ሳታደርሱ) ምቷቸውም። ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ። አላህ የበላይ ታላቅ ነውና።} [አንኒሳእ:34] እነዚህ ሶስቱ የሚፈፀሙት በቅደም ተከተል ነው እንጂ በአንዴ ሶስቱንም ፈፅሙ ማለት አይደለም። ከመምከርና ከመገሰፅ ይጀምራል። ከተሳካ ለአላህ ምስጋና ይገባው። ይህ ካልፈየደ በመኝታ ስፍራ ያገላታል። ይህም ካልፈየደ የበቀል ምት ሳይሆን ስርአት ማስያዣ ምት ይመታታል።

ወንድ ለቤተሰቡ ጠባቂ ነውና በጥበብና በመልካም ተግሳፅ ቤተሰቡን ሊያንፅና ምግባራቸውን ሊያጠራ ግዴታው ነው።

አዋቂ የሆነ ሰው የሰጠው ፈትዋ (ብይን) የሚያስከትለውና የሚያደርሰውን ችግር ስላወቀ የሰጠውን ብይን መከለስ እንደሚፈቀድለት እንረዳለን።

ጉዳት ባጋጠመ ወቅት ለመሪ ወይም ለአዋቂ ቅሬታን ማቅረብ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።

التصنيفات

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት, በትዳር ጥንዶች መካከል መኗኗር