እኔና ዱንያ ምን አገናኘን? እኔ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ትቷት እንደሄደ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለሁም።

እኔና ዱንያ ምን አገናኘን? እኔ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ትቷት እንደሄደ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለሁም።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰሌን ላይ ተኙ። ከተኙበት ሲነሱም ሰሌኑ ጎናቸው ላይ ሰንበር አውጥቷል። እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለርሶ ለስላሳ ፍራሽ ብናዘጋጅሎትስ?" አልን። እርሳቸውም: "እኔና ዱንያ ምን አገናኘን? እኔ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ትቷት እንደሄደ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለሁም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

ዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከአንድ በዘንባባ ነገር ተሰፍቶ በተሰራ ትንሽ ምንጣፍ ላይ ተኙና ሲነሱም ሰሌኑ የጎናቸው ቆዳ ላይ ሰንበር አወጣ። እኛም እንዲህ አልን: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለርሶ ለስላሳ ፍራሽ ብናዘጋጅሎት’ኮ በዚህ ሸካራ ሰሌን ላይ ከሚተኙ ይልቅ የተሻለ ይሆንሎታል።" ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "ከዱንያ ጋር ወደርሷ እስክማረክ ድረስ የሚያደርሰኝ ውዴታ የለኝም። የኔና እርሷ ውስጥ ያለኝ ቆይታ ምሳሌ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ዛፏን ትቶ እንደሚሄድ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለም።"

فوائد الحديث

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የነበሩበትን የዱንያ ቸልተኝነት ተገልጾ እንመለከታለን።

ሐዲሡ ውስጥ ዱንያ ውስጥ የግድ የሆነን ነገር መተው የሚጠቁም ነገር የለም። ሐዲሡ የሚጠቁመው ከአኺራ ተዘናግተን በርሷ መጠመድ እንደሌለብን ነው። ሰውዬው ዛፉን (ለጊዜውም ቢሆን) ወደሚፈልገው ስፍራ እንዲደርስ በመጠለያነት ተጠቅሞበታልና። ነገር ግን ዛፉ ላይ ጥገኛ አልሆነም።

ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሁኔታ ትምህርት መውሰድ ይገባናል። እርሳቸው መልካም አርአያ ናቸውና። ፈለጋቸውን የተከተለ ሰውም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ይመራልም ስኬትንም ያገኛል።

ሶሓቦች ረዺየሏሁ ዐንሁም ለአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ምቾት የነበራቸውን ጥረትና ለርሳቸው የነበራቸውን ውዴታ እንረዳለን።

በዳዕዋና ትምህርት በመስጠት ወቅት ምሳሌን መስጠት የተደነገገ ጉዳይ እንደሆነ እንረዳለን።

التصنيفات

ዱንያን ከመውደድ ማውገዝ, ነፍስን ማጥራት