إعدادات العرض
‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን…
‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›
ከአቡ ሑመይድ ወይም አቡ ኡሰይድ እንደተዘገበው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം తెలుగు Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Soomaali Shqip Српски Українська Wolof Tagalog Moore Malagasy தமிழ் Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገባ ወቅት የሚባለውን ዱዓ ለኡመታቸው ጠቆሙ። (አልላሁምመ ኢፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲክ) (አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) የእዝነትን ምክንያቶች ለርሱ እንዲያመቻችለት አላህን ይጠይቃል። ከመስጂድ ለመውጣት የፈለገ ጊዜም (አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ) (አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል። አላህን ከችሮታውና ከሐላል ሲሳዩ ተጨማሪ ፀጋዎቹን ይጠይቃል።فوائد الحديث
ወደ መስጂድ በሚገባ ወቅትና ከመስጂድ በሚወጣ ወቅት ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
ሲገባ እዝነትን በመጠየቅ ላይ ሲወጣ ደሞ ችሮታን በመጠየቅ ላይ የተገደበው: መስጂድ የሚገባ ሰው ወደ አላህና ወደ ጀነት በሚያቃርበው ነገሮች ላይ ነው የሚጠመደው ስለዚህ ከቦታው ጋር የሚስማማው እዝነትን መጠየቅ ነው። የወጣ ጊዜ ደሞ ከሲሳይ የአላህን ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ ስለሚሯሯጥ ከቦታው ጋር የሚስማማው ችሮታ መወሳቱ ነው።
እነዚህ ዚክሮች የሚባሉት መስጂድ መግባትና መውጣት ሲፈለግ እንደሆነ እንረዳለን።