የቁርአን ባለቤት የሆነ ሰው ምሳሌ የታሰረ ግመል ባለቤት አምሳያ ነው። ከተቆጣጠራት (በአግባቡ) ይይዛታል። ከለቀቃት ግን ትሄዳለች።

የቁርአን ባለቤት የሆነ ሰው ምሳሌ የታሰረ ግመል ባለቤት አምሳያ ነው። ከተቆጣጠራት (በአግባቡ) ይይዛታል። ከለቀቃት ግን ትሄዳለች።

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "የቁርአን ባለቤት የሆነ ሰው ምሳሌ የታሰረ ግመል ባለቤት አምሳያ ነው። ከተቆጣጠራት (በአግባቡ) ይይዛታል። ከለቀቃት ግን ትሄዳለች።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን የተማረ፣ በማንበብም ይሁን በቃል ሽምደዳ ማንበቡን ያዘወተረን ሰው ግመሉን ጉልበቷ ላይ በገመድ እንዳሰረ የግመል ባለቤት መሰሉት። ግመሏን በአግባቡ ከተቆጣጠረ እንደያዛት ይቀጥላል። ገመዱን ከፈታው ግን ግመሏ ትሄዳለችም ታመልጣለችም። የቁርአን ባለቤትም ካነበበው ያስታውሰዋል። ቁርአንን በአግባቡ ካልጠበቀ ግን ይረሳዋል። በአግባቡ ቁርአንን እስከተጠባበቀ ድረስም ሒፍዙም ከመኖር አይወገድም።

فوائد الحديث

ቁርአንን በመጠባበቅና በማንበብ ላይ መነሳሳቱንና ቁርአንን ለመርሳት መቃረብ ደግሞ መከልከሉን እንረዳለን።

ቁርአንን በመቅራት ላይ መዘውተር ምላስ ለቁርአን የተገራ እንዲሆንና ቁርአን ማንበብ እንዲቀል ያደርጋል። ቁርአንን የተወ ጊዜ ደግሞ ማንበብ ይከብደዋልም ይጠናበታልም።

ቃዲ እንዲህ ብለዋል: "(የቁርአን ባለቤት) ማለት ቁርአንን የተጎዳኘ ማለት ነው። ባለቤትነት ማለት መጎዳኘት ማለት ነው። ለዛም ነው እከሌ የእንትና ጓደኛ ነው፣ የጀነት ጓዶች፣ የእሳት ጓዶች የሚባለው።"

ከዳዕዋ ማድረጊያ መንገዶች መካከል አንዱ ምሳሌዎችን ማድረግ ነው።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ግመልን ለይተው የጠቀሱበት ምክንያት ከቤት እንስሳዎች ባጠቃላይ ከሰዎች እጅግ የምትፈረጥጥ እንስሳ ስለሆነች ነው። ከፈረጠጠችም በኋላ ለመያዝ አስቸጋሪ ስለሆነች ነው።"

التصنيفات

የቁርአን አቀራርና የመሸምደዱ ስነ-ስርዓቶች, የተከበረው ቁርአንን የማንበብ ስነ-ስርዓት