አንዱ በአንዱ ላይ በማይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን በማይተላለፍበት ልክ እንድትተናነሱ አላህ ወደኔ ራዕይ አውርዷል።

አንዱ በአንዱ ላይ በማይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን በማይተላለፍበት ልክ እንድትተናነሱ አላህ ወደኔ ራዕይ አውርዷል።

የበኒ ሙጃሺዕ ወንድም ከሆነው ከዒያድ ቢን ሒማር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ኹጥባ ለማድረግ ተነሱ። ከተናገሯቸው ንግግሮች መካከልም: "አንዱ በአንዱ ላይ በማይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን በማይተላለፍበት ልክ እንድትተናነሱ አላህ ወደኔ ራዕይ አውርዷል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለባልደረቦቻቸው ኹጥባ ለማድረግ ተነሱ። ከተናገሯቸው መካከልም: አላህ እንዲህ ብሎ ራዕይ ማውረዱን ተናገሩ: ሰዎች በዘራቸው ወይም በገንዘባቸው ወይም ከዛ ውጪ ባሉ ነገሮች አንዱ በአንዱ ላይ ልቅናን፣ ኩራትንና ክብርን ለራሱ በማድረግ ሳይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን ሳይተላለፍ ለፍጥረታት ራሳቸውን ዝቅ በማድረግና ማንነታቸውን በማለዘብ እርስ በርሳቸው መተናነሳቸው ግዴታ ነው።

فوائد الحديث

ከሐዲሡ ከምንወስዳቸው ቁምነገሮች መካከል በመተናነስ ላይ፣ ባለመኩራትና በሰዎች ላይ አለመንጠራራትን ያነሳሳል።

ወሰን ማለፍና መመፃደቅ መከልከሉን እንረዳለን።

ለአላህ መተናነስ ሁለት ትርጓሜዎች አሉት: የመጀመሪያው ትርጓሜ: ለአላህ ዲን መተናነስ ነው። ከእስልምና በላይ ራስን ከፍ አለማድረግ፣ እስልምናንና ህግጋቶቹን ከመፈፀም አለመኩራት ነው። ሁለተኛው: ለአላህ ብሎ ለአላህ ባሮች መተናነስ ነው። እነርሱን በመፍራትና እነርሱ ዘንድ ያለውን በመከጀል ሳይሆን ለአላህ ብቻ ብሎ ለነርሱ መተናነስ ነው።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር, የቀልብ ተግባራት