إعدادات العرض
እስልምና ላይ ሆኖ የሚበቃውን ያህል ሲሳይን የተለገሰና አላህ በሰጠውም የተብቃቃ ሰው በርግጥም ስኬታማ ሆኗል።
እስልምና ላይ ሆኖ የሚበቃውን ያህል ሲሳይን የተለገሰና አላህ በሰጠውም የተብቃቃ ሰው በርግጥም ስኬታማ ሆኗል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "እስልምና ላይ ሆኖ የሚበቃውን ያህል ሲሳይን የተለገሰና አላህ በሰጠውም የተብቃቃ ሰው በርግጥም ስኬታማ ሆኗል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili Hausa සිංහල ไทยالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ጌታው የተመራና ለእስልምና የተገጠመ፤ ምንም ሳይጨመርና ሳይቀነስ የሚበቃውን ያህል ሐላል ሲሳይ የተለገሰና አላህ በሰጠው ነገር እንዲወድና እንዲብቃቃ የተደረገ ሰው በርግጥም ስኬታማና እድለኛ መሆኑን ገለፁ።فوائد الحديث
ሰውዬው ደስታን የሚያገኘው እምነቱ ሲሟላ፣ ኑሮው በቂው ሲሆንና አላህ በሰጠው ነገር ሲብቃቃ ነው።
ከእስልምናና ሱና ጋር በዱንያ በተሰጠ ነገር በመብቃቃት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
التصنيفات
ዱንያን ከመውደድ ማውገዝ