ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።

ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጀነት ውስጥ ዛፍ እንዳለና ለውድድር የተዘጋጀንና ሲሮጥ ፈጣን የሆነን ፈረስ የሚጋልብ ሰው በዛፉ ስር መቶ አመት ጋልቦም የመጨረሻ ቅርንጫፉ ጋር እንደማይደርስ ተናገሩ።

فوائد الحديث

የጀነት ስፋትና የዛፎቿ ትልቀት መገለፁን እንረዳለን።

التصنيفات

የጀነትና እሳት ባህሪዎች