إعدادات العرض
አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።
አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kurdî Português සිංහල Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Română ไทยالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በስንፍና ወይም በጥጋብና በመሳሰሉት ምክንያት ሲያዛጋ አፉን የከፈተ ሰው ክፍት እንደሆነ ከተወው ሸይጧን ወደ ውስጡ ይገባልና እጁን አፉ ላይ በማኖር እንዲዘጋው ተናገሩ። እጁን አፉ ላይ ማኖሩ ሲያፋሽግ ሸይጧን እንዳይገባ ይከላከላልና።فوائد الحديث
አንድ ሰው ማዛጋት የፈለገ ጊዜ በቻለው መጠን አፉን መክደን አለበት። ይህም አፉ እንዳይከፈት አፉን ተቆጣጥሮ እንደተዘጋ እንዲቀር በማድረግ ነው። አፉ እንደተዘጋ ማስቀረት ካልቻለም እጁን አፉ ላይ በማኖር በእጁ አፉን መሸፈን ነው።
በሁሉም ሁኔታዎች ኢስላማዊ ስነ-ስርዓቶችን መጠበቅ ይገባል። ይህም የሙሉነትና የስነምግባር መገለጫ ስለሆነ ነው።
ሸይጧን ወደ ሰው ልጅ ከሚገባበት ቀዳዳ ባጠቃላይ መጠንቀቅ ይገባል።
التصنيفات
የማስነጠስና የማዛጋት ስነ-ስርዓት