إعدادات العرض
“የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።
“የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ “የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።"
الترجمة
العربية Tagalog Português دری অসমীয়া বাংলা Kurdî پښتو Hausa Tiếng Việt Македонски O‘zbek Kiswahili ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ Moore తెలుగు اردو Azərbaycan ไทย Magyar Türkçe ქართული 中文 ಕನ್ನಡ ગુજરાતી Українська Shqip हिन्दी Кыргызча Српски Kinyarwanda тоҷикӣ Wolof Čeština Русский Bahasa Indonesia English தமிழ் नेपाली മലയാളം kmr فارسی Bambara ms Bosanski Lietuviųالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የአንድ ሙስሊም እስልምና በተሟላ መልኩ የሚያምረውና ኢማኑ የሚሞላው ከማያገባው፣ ከማይመለከተው፣ ከማይጠቅመውና ከማያሳስበው ንግግርና ተግባር ወይም ከማይመለከተው ዲናዊና ዱንያዊ ጉዳይ ሲርቅ እንደሆነ ገለፁ። አንድ ሰው በማይመለከተው ነገር መጠመዱ ምናልባት ከሚጠቅመው ነገር ያዘናጋዋል ወይም መራቅ የሚገባውን ነገር እንዲፈፅም ይዳርገዋል። የሰው ልጅ የትንሳኤ ቀን ስለስራዎቹ ተጠያቂ ነውና።فوائد الحديث
ሰዎች በእስልምና ደረጃቸው ይበላለጣሉ። በአንዳንድ ተግባራት የእስልምና ውበት ይጨምራል።
ዛዛታ፣ ትርፍ ንግግሮችንና ከንቱ ተግባራትን መተው የሰውዬውን እስልምና መሙላት የሚጠቁም ነው።
ሁሉም ሰው ለዲኑና ለዱንያው በሚጠቅመው ጉዳይ ላይ እንዲጠመድ መነሳሳቱን እንረዳለን። የሰውዬው እስልምና የሚዋበው የማይጠቅመውን ሲተው ከሆነ የእስልምናው ውበት የሚጨምረው ደግሞ በሚጠቅመው ላይ በመጠመዱ ነው ማለት ነው።
ኢብኑል ቀይዪም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ በማለት በአንድ ንግግር ጥንቁቅነትን በሙሉ ጠቅልለው ገለፁት: "የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።" ይህም የማይጠቅምን ንግግር፣ እይታ፣ መስማት፣ መጨበጥ፣ መጓዝ፣ ማሰብና ሌሎችንም ውጫዊና ውስጣዊን እንቅስቃሴን መተው ያቀፈ ንግግር ነው። ይህቺ ንግግር ጥንቁቅነት ለመግለፅ ፍቱን የሆነች ቃል ናት።»
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከአደብ መሰረቶች መካከል አንዱ መሰረት ነው።"
የሰው ልጅ የሚጠቅመውንና የማይጠቅመውን የሚያውቀው በመማር ስለሆነ በዚህ ሐዲሥ እውቀትን መፈለግ ተበረታቷል።
በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከልና ሰውን መምከር ትእዛዝ የተላለፈበት ጉዳይ ስለሆነ ለሰው ከሚጠቅሙ ነገሮች መካከል የሚመደቡ ናቸው።
የሐዲሡ ጥቅል ሃሳብ ውስጥ ከሚካተቱ ነገሮች መካከል: አላህ ዐዘ ወጀል ከከለከላቸው፣ ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የጠሉት ነገር የማይጠቅሙ ስለሆኑ መራቅ እንደሚያስፈልግ ነው። ልክ እንደዚሁ የማያስፈልጉ የመጪው አለም ጉዳዮችን እንደሩቅ እውቀት እውነታ፣ ስለ አላህ የመፍጠር ሂደትና ትእዛዛት ጉዳይ በዝርዝር ማጥናት፣ ስለ አላህ ቅድመ ውሳኔ ጉዳዮች መጠየቅና መመራመር፣ ያልተከሰቱን ወይም ከነአካቴው ሊከሰቱ ስለማይችሉ ነገሮች ቢከሰቱስ ብሎ መጠመድ የሐዲሡ ጥቅል ውስጥ የሚካተቱ የማይጠቅሙ ጉዳዮች ናቸው።
التصنيفات
ውግዝ ስነ-ምግባር