አንድም መከራ አጋጥሞት አላህ እንዳዘዘው ‹{ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] አልላሁመእጁርኒ ፊ ሙሲበቲ፣ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ› የሚል ሙስሊም የለም አላህ ከዛ…

አንድም መከራ አጋጥሞት አላህ እንዳዘዘው ‹{ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] አልላሁመእጁርኒ ፊ ሙሲበቲ፣ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ› የሚል ሙስሊም የለም አላህ ከዛ የተሻለ ነገር ቢተካለት እንጂ።

ከአማኞች እናት ከኡሙ ሰለማ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "አንድም መከራ አጋጥሞት አላህ እንዳዘዘው ‹{ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] አልላሁመእጁርኒ ፊ ሙሲበቲ፣ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ› የሚል ሙስሊም የለም አላህ ከዛ የተሻለ ነገር ቢተካለት እንጂ።"» ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: "አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለና?! ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ይህንን ዱዓ አልኩኝ። አላህም ለኔ የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።" ትርጉሙም ({እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} [አልበቀራ:156] አላህ ሆይ በመከራዬ ምንዳን ስጠኝ። ከደረሰበኝ መከራ የተሻለንም ተካልኝ።) ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች እናት ኡሙ ሰለማ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - አንድ ጊዜ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ እንደሰማች አወሳች: አንድም መከራ የሚደርስበትና አላህ ለርሱ የመረጠለትን ይህንን ውዳሴ የሚል ሙስሊም የለም: {ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] ትርጉሙም {እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} (አላሁመእጁርኒ) አላህ ሆይ! በደረሰበኝ መከራ የትእግስቴን ምንዳ ስጠኝ! (ፊ ሙሲበቲ) (ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ) ከርሱ የተሻለንም ለኔ ተካልኝ አይልም አላህ ለርሱ ከደረሰበት መከራ የተሻለን ቢለውጥለት እንጂ። ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: "ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለ? ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ግን አላህ አግዞኝ ይህንን ውዳሴ ተናገርኩት። አላህም ለኔ ከአቡ ሰለማ የተሻሉትን የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።"

فوائد الحديث

መከራ በሚያጋጥም ወቅት ባለመበሰጫጨትና ትእግስት በማድረግ መታዘዙን እንረዳለን።

መከራ በሚያጋጥም ወቅት አላህ ዘንድ ምትኩ ስላለ ዱዓእ በማድረግ ወደ አላህ መዞር እንደሚገባ እንረዳለን።

አንድ አማኝ የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትእዛዝ ጥበቡ ባይታየው እንኳ የርሳቸውን ትእዛዝ መፈፀም አስፈላጊነቱን እንረዳለን።

የተሟላ መልካም የሚባለው አንድ አማኝ የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትእዛዝ ሲተገብር ነው።

التصنيفات

የነቢዩ ቤተሰቦች ደረጃ, የቀልብ ተግባራት