አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።

አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።

ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ የትንሳኤ ቀን ለሒሳብ ብሎ የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ ከአላህ ጋር ወይም ከሰዎች ጋር ሊሞላው ቃል የገባውን ቃል ኪዳን ላልሞላ ከዳተኛ ሁሉ ከዳተኝነቱ የሚጋለጥበት አርማ ይተከላል። በዛን እለትም በአርማው ላይ እንዲህ ተብሎ ይለፈፋል: "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የከዳው ክዳት ነው።" ይህም የትንሳኤ ቀን ለተሰበሰቡ ሰዎች መጥፎ ስራውን ለማሳየት ነው።

فوائد الحديث

ክዳትን በማስመልከት ይህ ከባድ ዛቻ ስለመጣ ክዳት ክልክል መሆኑንና ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል መሆኑንም እንረዳለን።

በደሙ ወይም በክብሩ ወይም በምስጢሩ ወይም በገንዘቡ አምኖህ ላንተ የሰጠውን እምነት መክዳት ይህ ሁሉ የተዛተበት ክዳት ውስጥ ይካተታል።

ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ለዐረቦች መነገሩ ተመሳሳዩን ይሰሩት የነበረው ድርጊት ስለነበር ነው። እነርሱ ቃሉን ለሚሞላ ነጭ ባንዲራ ይተክሉለት ነበር። ለከዳተኛ ደግሞ እርሱን ለማውገዝና ለመውቀስ ጥቁር ባንዲራ ይተክሉ ነበር። ሐዲሡም ለከዳተኛ ተመሳሳይ ነገር እንደሚደረግ አስፈረደ። ይህም የትንሳኤ ቀን ባህሪው ታውቆ የትንሳኤ ቀን የቆሙ ሰዎች እንዲያወግዙት ነው።"

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ የትንሳኤ ቀን ሰዎች በአባቶቻቸው እንደሚጠሩ ማሳያ ነው። ይህም ሐዲሡ ውስጥ "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነት ነው።" ይባላል ስላሉ ነው።»

التصنيفات

ውግዝ ስነ-ምግባር, የጂሃድ ስነ-ስርዓት