መስካችሁ ላይ ሙጥኝ አትበሉ ዱንያን ትከጅላላችሁና።

መስካችሁ ላይ ሙጥኝ አትበሉ ዱንያን ትከጅላላችሁና።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "መስካችሁ ላይ ሙጥኝ አትበሉ ዱንያን ትከጅላላችሁና።"»

[Hasan/Sound by virtue of corroborating evidence] [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የአትክልትና የእርሻ (የስራ) መስክ ላይ ሙጥኝ ማለትን ከለከሉ። ይህም ዱንያን ለመከጀልና ከአኺራ ይልቅ ወደ ዱንያ እንዲዘነበል ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ነው።

فوائد الحديث

ከአኺራ የሚያዞር በሆነ መልኩ ዱንያን ሙጥኝ ማለት መከልከሉን እንረዳለን።

ሐዲሡ ውስጥ የተከለከለው ለመኖሪያ የሚሆን የገቢ ምንጭ መያዝ አይደለም። የተከለከለው ዱንያ ውስጥ መስመጥና አኺራን መርሳት ነው።

ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "በሐዲሡ የተፈለገው: አላህን ከማስታወስ ስለሚያዘናጋችሁ የስራ መስካችሁን በመያዝ አትስመጡ ማለት ነው።"

التصنيفات

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት, ዱንያን ከመውደድ ማውገዝ