የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።

የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሽማግሌ ሰውነቱ ቢጃጅና ቢደክምም ቀልቡ ግን ሁለት ነገሮችን በመውደድ በኩል ወጣት መሆኗን ተናገሩ: የመጀመሪያው: ገንዘብን በማብዛት ዱንያን መውደድ ነው። ሁለተኛው: ረጅም ህይወትን፣ እድሜን፣ ምቾትና ምኞትን መውደድ ነው።

فوائد الحديث

የሰው ልጅ የተፈጠረበት ባህሪው መገለፁ፤ ይሀውም ዱንያን መውደድና ምኞትን ማርዘም ነው።

ምኞትን ማርዘምና ገንዘብ ማጠራቀም ላይ መጓጓት የተወገዘ መሆኑ መጠቆሙ፤ ይህም ለሞት መዘጋጀትን እንደሚገባ፤ ሀብታም የሆነ ሰው ሶደቃ መስጠቱ ያለው ደረጃ፣ ድሃ የሆነ ሰው ደግሞ መብቃቃቱ ያለውን ደረጃ መረዳት እንደሚገባ ያስፈርዳል።

የሰው ልጅ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ነገር ነፍሱ ናት። ምንግዜም እንድትቆይለት ይፈልጋል። ስለዚህም እድሜው መርዘሟን ወደደ፤ ጤንነቱና መደሰቻዎቹ እንዲዘወትሩለት የሚያደርገው ትልቁ ምክንያት ደሞ ገንዘብ ስለሆነ ገንዘብንም ወደደ፤ ጉዳዩ በቅርቡ እንደሚያጣው በተሰማው ልክ ውዴታውና እንዲዘወትርለት ያለው ፍላጎትም በዛው ልክ ይበረታል።

التصنيفات

ዱንያን ከመውደድ ማውገዝ