ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።

ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።

ከዐብደላህ ቢን ሚሕሰን አልአንሷሪይ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።"

[ሐሰን ነው።] [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከናንተ ከሙስሊሞች መካከል ሰውነቱን ከበሽታና ህመም ጤነኛና ደህና ሆኖ፤ በነፍሱ፣ በቤተሰቡ፣ በዘመዶቹና በመንገዱ ላይ ሁሉ ሳይፈራ ደህንነቱ የተጠበቀለት ሆኖ፤ እርሱ ዘንድ በቂ ሐላል የሆነ የቀን ቀለብ ኑሮት ያነጋ ሰው ዱንያ ባጠቃላይ ለርሱ እንደተሰበሰበችለት አምሳያ መሆኑን ተናገሩ።

فوائد الحديث

የሰው ልጅ ጤንነት፣ ደህንነትና ቀለብ የግድ እንደሚያስፈልገው መገለፁን እንረዳለን።

አንድ ባሪያ በነዚህ ፀጋዎች አላህን ማመስገንና ማወደስ እንደሚገባው እንረዳለን።

ከዱንያ ቸልተኛ በመሆንና በመብቃቃት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

التصنيفات

ዱንያን ቸል ማለት (ዙህድ)ና ጥንቁቅነት