إعدادات العرض
ከናንተ በታች ወዳለ ሰው ተመልከቱ እንጂ ከናንተ በላይ ወዳለ ሰው አትመልከቱ! ይህን ማድረጋችሁ (የበታቻችሁን ማየት) አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ አሳንሶ ከማየት ይታደጋችኃል።
ከናንተ በታች ወዳለ ሰው ተመልከቱ እንጂ ከናንተ በላይ ወዳለ ሰው አትመልከቱ! ይህን ማድረጋችሁ (የበታቻችሁን ማየት) አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ አሳንሶ ከማየት ይታደጋችኃል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ በታች ወዳለ ሰው ተመልከቱ እንጂ ከናንተ በላይ ወዳለ ሰው አትመልከቱ! ይህን ማድረጋችሁ (የበታቻችሁን ማየት) አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ አሳንሶ ከማየት ይታደጋችኃል።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili සිංහල ไทยالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙስሊም የሆነ ሰው በዱንያ ጉዳዮቹ፣ በማዕረግ፣ በገንዘብ፣ በክብርና በሌሎችም ነገሮች በአንፃራዊ ሁኔታው ዝቅ ወዳለ ሰው እንዲመለከትና በዱንያዊ ጉዳዮች ደሞ ከርሱ የበላዩና በዱኒያ የሚበልጠው ወደሆነ ሰው እንዳይመለከት አዘዙ። ከርሱ በታች ወደሆነ ሰው መመልከት አላህ የዋለልህን ፀጋ እንዳታሳንስና ዝቅ እንዳታደርግ የሚያግዝ ነው።فوائد الحديث
መብቃቃት ከትላልቅ የአማኞች ስነምግባር መካከል አንዱ ነው። መብቃቃት በአላህ ውሳኔ የመውደድም ምልክት ነው።
ኢብኑ ጀሪር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የመልካም አይነቶችን ባጠቃላይ የሚሰበስብ ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ በዱንያ የሚበልጡትን የተመለከተ ጊዜ ነፍሱ እንደነርሱ አምሳያ መሆንን ትፈልጋለችና። እርሱ ዘንድ ያለውን የአላህን ፀጋም ያሳንሳል። የበለጡት ጋር ለመድረስ ወይም ለመቀራረብና ተጨማሪን ለማግኘትም ይጓጓል። ይህም አብዛኛው ሰዎች ላይ የሚስተዋል ነው። ነገር ግን በዱንያዊ ጉዳዮች የበታቾቹን የተመለከተ ጊዜ አላህ የዋለለትን ፀጋ በማስተዋል ያመሰግነዋልም ራሱንም ዝቅ ያደርጋል። በተሰጠው ፀጋም መልካሙን ይሰራበታል።"
التصنيفات
ነፍስን ማጥራት