إعدادات العرض
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ…
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል ዐርሺል ከሪም" (ትርጉሙም፡ "ከታላቁና ቻይ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ፣ ከተከበረው ዐርሽ ጌታ አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" ማለት ነው።)
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል ዐርሺል ከሪም" (ትርጉሙም፡ "ከታላቁና ቻይ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ፣ ከተከበረው ዐርሽ ጌታ አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" ማለት ነው።)
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල Kurdî Português Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Hausa Nederlands മലയാളം Română ไทย Magyar ქართულიالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ችግርና ጭንቀት በርሳቸው ላይ በሚበረታ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። "ታላቅ በሆነው" ክብሩ፣ በማንነቱ፣ በባህሪውና በድርጊቱ ነገሩ የላቀ፤ "ቻይ" ወንጀለኛን በመቅጣት የማይቸኩል ይልቁንም የሚያዘገይ፤ መቅጣት እየቻለ ይቅር የሚል፤ በሁሉም ነገር ላይም ቻይ የሆነ ነው። "ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የታላቁ ዐርሽ ፈጣሪ ነው። "የሰማያትና የምድር ጌታ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የሰማያትና ምድር ፈጣሪ፤ በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረ፤ ባለቤቱ፣ አስተካካዩና እንደፈለገው የሚያስተናብረው ነው። "የተከበረው ዐርሽ ጌታ" የተከበረውን ዐርሽ የፈጠረ ነው።فوائد الحديث
መከራና ችግር ሲያጋጥም በዱዓ ወደ አላህ መዋደቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በችግር ወቅት በዚህ ዚክር ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
የበላይ የሆነው አላህ በላዩ ላይ ከፍ ያለበት የአርረሕማን ዐርሽ ከፍጡራን ባጠቃላይ ከፍ ያለ፤ ትልቁና ግዙፉ ፍጡር ነው። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱ ትልቅና የተከበረ መሆኑን ገልፀዋል።
ሰማይና ምድር ተለይተው የተጠቀሱበት ምክንያት ከሚታዩ ፍጡሮች ባጠቃላይ ትላልቆቹ ስለሆኑ ነው።
ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህንን ውዳሴ አላህን በጌትነቱ አውስተው የጀመሩት ችግሩ እንዲወገድ ተስማሚው ስም ስለሆነ ነው። የጌታነት ማንነቱ ችግርን ማስወገድ ያስፈርዳልና። እዚህ ውዳሴ ውስጥ ተውሒድን ያካተተችው፣ የበላይነቱን (ግርማውን) የማጥሪያ መሰረት የሆነችው ላኢላሃ ኢለሏህም አለች፤ የችሎታውን ምሉዕነት የምትገልፀው ልቅናውን ታመላክታለች፤ "አልሒልም" ዕውቀቱን የምትጠቁመው ቻይነቱን (እያወቀና እየቻለም አለመቅጣቱ) ትገልፃለች። ምክንያቱም የማያውቅ አካል ቻይነት "ሒልም" እና ቸርነት አለው ተብሎ አይታሰብምና። እነዚህ ሁለቱ ባህሪያት ደሞ የመከበሪያ ባህሪያቶች መሰረት ናቸው።
التصنيفات
በጭንቅ ወቅት የሚባሉ ዚክሮች