إعدادات العرض
የምትረዱትና የምትቀለቡት በደካሞቻችሁ ሰበብ አይደለምን?
የምትረዱትና የምትቀለቡት በደካሞቻችሁ ሰበብ አይደለምን?
ከሙስዐብ ቢን ሰዕድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ሰዕድ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ደረጃ እንዳለው ተሰማው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉት: "የምትረዱትና የምትቀለቡት በደካሞቻችሁ ሰበብ አይደለምን?"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል። - ቲርሚዚ ዘግበውታል። - An-Nasaa’i - አቡዳውድ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Nederlands Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ራሱን በጀግንነትና በመሳሰሉት ምክንያት ከርሱ በታች ካሉ ደካማ ሰዎች የበለጠ አድርጎ አሰበ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "በደካሞቻችሁ፣ በነርሱ ዱዓ፣ ሶላትና ኢኽላስ ካልሆነ በቀር ትረዳላችሁን? ትቀለባላችሁን?" አሉ። አብዛኛው ጊዜ ደካማዎች ዱዓቸውን እጅግ ለአላህ አጥርተው፣ አምልኳቸውንም እጅግ ተመስጠው ነው የሚፈፅሙት። ይህም ቀልባቸው በዱንያ ጌጣጌጥ ከመንጠልጠል የፀዳ ስለሆነ ነው።فوائد الحديث
በመተናነስ ላይ መነሳሳቱንና በሌሎች ላይ ከፍ ከፍ ከማለት መከልከሉን እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ጠንካራው በጀግንነቱ ስለሚሻል ከደካሞች ቢበልጥ ደካማው ደግሞ በዱዓውና ስራውን ለአላህ አጥርቶ በመስራቱ ስለሚሻል ከጠንካራው ይበልጣል።"
ለድሃዎች በጎ በማድረግና ሐቃቸውን በመስጠት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህን ማድረግህ አላህ እንዲያዝንልህና እንዲረዳህ የሚያደርግ አንዱ ምክንያት ነውና።
التصنيفات
የደጋጎች ሁኔታ