እናንተ የምትፈልጉትን ምግብና መጠጥ እየተመገባችሁ አይደልንዴ? ነቢያችሁን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሆዳቸውን የሚሞሉበት የሆነ የወረደ ተምርን እንኳ ሳያገኙ…

እናንተ የምትፈልጉትን ምግብና መጠጥ እየተመገባችሁ አይደልንዴ? ነቢያችሁን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሆዳቸውን የሚሞሉበት የሆነ የወረደ ተምርን እንኳ ሳያገኙ ቀርተው ተመልክቻቸዋለሁ።

ከኑዕማን ቢን በሺር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "እናንተ የምትፈልጉትን ምግብና መጠጥ እየተመገባችሁ አይደልንዴ? ነቢያችሁን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሆዳቸውን የሚሞሉበት የሆነ የወረደ ተምርን እንኳ ሳያገኙ ቀርተው ተመልክቻቸዋለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ኑዕማን ቢን በሺር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሰዎች ያሉበት ፀጋ የፈለጉትን ያህል የሚበሉና የሚጠጡበት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልፀው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ግን ረሃባቸውን ለማስታገስ ሆዳቸውን የሚሞላ የወረደ ተምርን እንኳ የማያገኙበት ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ተናገረ።

فوائد الحديث

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የነበሩበትን የዱንያ ዛሂድነት (ቸልተኝነት) መገለፁ።

ከዱንያ ዛሂድ (ቸልተኛ) በመሆን፣ ዱንያን በማሳነስና ነቢዩን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመከተል ላይ መነሳሳቱን እንመለከታለን።

ሰዎች ያሉበትን ፀጋ በማስታወስና አላህንም በማመስገን ላይ መተዋወስ እንደሚገባ መነሳሳቱን እንረዳለን።

التصنيفات

ዱንያን ከመውደድ ማውገዝ