إعدادات العرض
ሶስት አይነት ሰዎች አላህ የትንሳኤ ቀን አያናግራቸውም። ከወንጀላቸውም አያጠራቸውም። ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው።
ሶስት አይነት ሰዎች አላህ የትንሳኤ ቀን አያናግራቸውም። ከወንጀላቸውም አያጠራቸውም። ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው።
ከሰልማን አልፋሪሲይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሶስት አይነት ሰዎች አላህ የትንሳኤ ቀን አያናግራቸውም። ከወንጀላቸውም አያጠራቸውም። ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው። የሽማግሌ ዝሙተኛ፣ የድሃ ኩራተኛና አላህን ሸቀጡ ያደረገ ሰው ነው። ያለመሃላ አይሸጥም። ያለመሃላው አይገዛም።"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Русский Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የትንሳኤ ቀን ተውበት እስካላደረጉ ወይም አላህ ቅጣቱን ይቅር እስካላላቸው ድረስ ቅጣት ስለሚገባቸው ሶስት የሰዎች አይነት ተናገሩ። የመጀመሪያው ቅጣት: የትንሳኤ ቀን አላህ በጣም ስለሚቆጣባቸው አያናግራቸውም። ይልቁንም እነርሱን ችላ ይላል። ወይም በነርሱ ላይ መቆጣቱን የሚጠቁም የማያስደስታቸውን ንግግር ያናግራቸዋል። ሁለተኛው ቅጣት: አያጠራቸውም፣ በነርሱ ላይ አያወድስም፣ ከወንጀላቸውም አያጠራቸውም። ሶስተኛው ቅጣት: በመጪው አለም አሳማሚና ብርቱ ቅጣት አላቸው። እነዚህም ሰዎች: የመጀመሪያው: ዝሙት ላይ የሚወድቅ ያረጀ ሰውዬ ነው። ሁለተኛው: ገንዘብ የሌለው ድሃ ከመሆኑም ጋር ሰዎች ላይ ይኮራል። ሶስተኛው: ሲሸጥና ሲገዛ በአላህ መማል የሚያበዛ ሰው ነው። በዚህም የአላህን ስም ዝቅ ያደርጋል። የአላህን ስምም ገንዘብ ማግኛ ያደርገዋል።فوائد الحديث
ቃዲ ዒያድ የዚህን ከባድ ቅጣት ምክንያት ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል: "የተጠቀሱት እያንዳንዳቸው ከወንጀሉ ጋር ቅርርብ የሌላቸው ከመሆናቸውም ጋር፣ የሚያስገድዳቸው ካለመኖሩም ጋርና፣ ወደ ወንጀሉ የሚገፋፋቸው ሳይኖር ነው ወንጀሉን የፈፀሙት። ማንም ሰው ወንጀልን ለመፈፀም በቂ ምክንያት ባይኖረውም ነገር ግን ወደዚህ ወንጀል የሚያስገድድና በተለምዶ የሚገፋፋ ነገር ሳይኖረው መስራቱ ትዕቢት፣ የአላህን ሐቅ አቅልሎ ማየትና ያለምንም ፍላጎት ወንጀልን አልሞ መስራት ይመስልበታል።"
ዝሙት፣ ውሸትና ኩራት ከትላልቅ ወንጀል መሆኑን እንረዳለን።
ኩራት ማለት: እውነትን መመለስና ፍጡራንን ማሳነስ ነው።
ሲሸጥና ሲገዛ መሃላን አብዝቶ መጠቀም መከልከሉንና መሃላን በማክበርና የአላህን ስሞች በማክበር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። አላህ እንዲህ ብሏል::{አላህን ለመሃላዎቻችሁ ግርዶ አታድርጉ።} [አልበቀራህ:32]
التصنيفات
ወንጀለኞችን ማውገዝ