አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።

አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።" አቡ ሰዒድም በዚህች ንግግር ተደሰተና እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በድጋሚ ይንገሩኝ!" እርሳቸውም ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉ: "ሌላም አንድ ስራ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ ይደረጋል። በየሁሉም ደረጃ መካከልም ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በአላህ ያመነና በጌትነቱ፣ በአምላክነቱ፣ በንጉስነቱ፣ በአለቃነቱ በአዛዥነቱ የወደደ፤ በእስልምና ሃይማኖትነት የወደደና በአጠቃላይ ትእዛዛቶችና ክልከላዎቹ የተመራና እጅ የሰጠ፤ በሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ነቢይነትና ይዘውት በመጡትና ባደረሱት ነገር ሁሉ የወደደ ሰው ጀነት ለርሱ ፀንታለታለች አሉት። አቡ ሰዒድም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዚህች ንግግር በመደሰት "ድገሙልኝ የአላህ መልክተኛ" አላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉት: "እኔ ዘንድ ሌላ ጉዳይ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ የሚደረግባት የሆነች፤ በየሁሉም ደረጃ መካከል ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" አቡ ሰዒድም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።

فوائد الحديث

ጀነት መግባትን ከሚያረጋግጡ ነገሮች መካከል በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነትና በሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነቢይነት መውደድ አንዱ ነው።

በአላህ መንገድ የመታገል ጉዳይ ትልቅነቱን እንረዳለን።

በአላህ መንገድ የሚታገል ሰው ጀነት ውስጥ ያለው ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን እንረዳለን።

ጀነት ውስጥ ተቆጥረው የማያልቁ ደረጃዎችና እርከኖች አሉ። በአላህ መንገድ ለሚታገሉም መቶ ደረጃዎች አላቸው።

የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦች መልካምን፣ ወደ መልካም መግቢያ መንገዶችና ምክንያቶችን ለማወቅ ያላቸውን ውዴታ እንረዳለን።

التصنيفات

የጀነትና እሳት ባህሪዎች, የጂሃድ ትሩፋት