إعدادات العرض
ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።
ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።
ከዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "እኔ ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድን ሐዲሥ የሰማሁ ጊዜ አላህ በዛ ሐዲሥ በሻው መንገድ የሚጠቅመኝ ሰው ነበርኩ፤ ከሶሐቦቻቸው መካከል አንድ ሰው ሐዲሥ የነገረኝ ጊዜ ታዲያ አስምለዋለሁ። ከማለልኝ አምነዋለሁ። አቡበከር ለኔ አንድ ሐዲሥ ነግሮኛል። አቡበከር የነገረኝም እውነት ነበር። አቡበከር እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።› ቀጥለውም ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት} [ኣሊ ዒምራን:135] '"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە සිංහල हिन्दी Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Türkçe Tiếng Việt नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Bosanski Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Kurdî Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip Português ქართული Azərbaycan 中文 Magyar فارسیالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከወንጀሉ ወደ አላህ በመመለስ ኒያ ቁሞ ሁለት ረከዓ ሰግዶ ከዚያም አላህን ምህረት የሚጠይቅ አንድም ኃጢዓት የሚሰራ ባሪያ እንደሌለ ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን የአላህ ቃል አነበቡ: {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ከአላህም ሌላ ኀጢዐቶችን የሚምር አንድም የለ። (በስህተት) በሰሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት (ተደግሳለች)።} [ኣሊ ዒምራን:135]فوائد الحديث
ሶላት ላይ እና ለወንጀል ምህረት መጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
የአላህ ምህረት ሰፊ መሆኑንና፤ ተውበትና ምህረት ሲጠየቅ እንደሚቀበል እንረዳለን።
التصنيفات
ተውበት