እነዚያን በዱንያ ውስጥ ሰዎችን የሚቀጡን ሰዎች አላህ ይቀጣቸዋል።

እነዚያን በዱንያ ውስጥ ሰዎችን የሚቀጡን ሰዎች አላህ ይቀጣቸዋል።

ከሂሻም ቢን ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: ሂሻም በሻም ውስጥ በሚገኙ ዐረብ ባልሆኑ ገበሬዎች ፀሐይ ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ሰዎች በኩል አለፈ። እርሱም: "ምን ሆነው ነው?" አለ። ሰዎችም "ግብር ባለመክፈላቸው ለቅጣት እዚሁ ታስረው ነው።" ብለው መለሱለት። ሂሻምም «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ እንደሰማው እመሰክራለሁ: "እነዚያን በዱንያ ውስጥ ሰዎችን የሚቀጡን ሰዎች አላህ ይቀጣቸዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ሂሻም ቢን ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ዐረብ ባልሆኑ ገበሬዎች በኩል ሲያልፍ ከፀሐይ ሐሩር በታች እንዲቆሙ ተደርገው ተመለከተ። ስለ ሁኔታቸውም ጠየቀ። ይህ የተደረገባቸው ግብር መክፈል እየቻሉ ባለመክፈላቸው እንደሆነም ተነገረው። ሂሻምም -አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና- ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ እንደሰማው እመሰክራለሁ አለ: አላህ ያለ አግባብ በግፍ በዱንያ ውስጥ ሌሎችን የሚቀጡ ሰዎችን ይቀጣቸዋል።

فوائد الحديث

ጂዝያ (ግብር) ማለት: የመጽሐፍ ሰዎች ሆነው አቅመ አዳም በደረሱና ሀብታም በሆኑ ወንዶች ላይ በሙስሊሞች አገር ስለሚኖሩና ስለተሰጣቸው ከለላ እንዲከፍሉ የሚመደብባቸው ገንዘብ ነው።

ያለ ሸሪዓዊ አስገዳጅ ምክንያት ከሃዲን እንኳን ቢሆን ሰዎችን መቅጣት ክልክል እንደሆነ እንረዳለን።

በዳዮች ለበደላቸው እንደተዛተባቸው እንረዳለን።

የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባልደረቦች በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከልን እንዴት አጥብቀው ይተገብሩ እንደነበር እንረዳለን።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የሚተረጎመው ያለ አግባብ በመቅጣት ነው። እንደ ቂሷስ (የገደለን መግደል)፣ (ሑዱድ) የሸሪዓዊ መቀጮዎችን ማስፈፀም፣ ስርዓት ለማስያዝ መቅጣትና የመሳሰሉት አግባብ የሆኑ ቅጣቶችን መቅጣት ሐዲሡ ውስጥ አይካተትም።"

التصنيفات

ውግዝ ስነ-ምግባር