የሰው ልጅ እንደሆዱ መጥፎን ቋት አልሞላም። የአደም ልጅ ወገቡን ቀና የሚያደርጉለት ጥቂት ጉርሻዎች ይበቁታል። (መጥገቡ) የማይቀር ከሆነ (የሆዱን) ሲሶውን ለምግቡ፣ ሲሶውን ለመጠጡ፣…

የሰው ልጅ እንደሆዱ መጥፎን ቋት አልሞላም። የአደም ልጅ ወገቡን ቀና የሚያደርጉለት ጥቂት ጉርሻዎች ይበቁታል። (መጥገቡ) የማይቀር ከሆነ (የሆዱን) ሲሶውን ለምግቡ፣ ሲሶውን ለመጠጡ፣ ሲሶውን ለትንፋሹ ያድርግ።

ከሚቅዳም ቢን መዕዲከሪበ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልዕክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "የሰው ልጅ እንደሆዱ መጥፎን ቋት አልሞላም። የአደም ልጅ ወገቡን ቀና የሚያደርጉለት ጥቂት ጉርሻዎች ይበቁታል። (መጥገቡ) የማይቀር ከሆነ (የሆዱን) ሲሶውን ለምግቡ፣ ሲሶውን ለመጠጡ፣ ሲሶውን ለትንፋሹ ያድርግ።"

[ሶሒሕ ነው።] [رواه الإمام أحمد والترمذي والنسائي وابن ماجه]

الشرح

የተከበሩት ነቢይ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከህክምና መሰረቶች አንዱን መሰረት ጠቆሙን። ይህም የሰው ልጅ ጤናውን የሚጠብቅበት መጠበቂያ ነው። እሱም አመጋገብን ማሳነስ ነው። እንደውም አንጀቱን የሚዘጋለትን ያህልና የግዴታ ስራዎቹ ላይ የሚያበረታውን ያህል ይመገብ። ከሚሞሉ ቋቶች ሁሉ መጥፎው ሆድ ነው። ይህም በመጥገቡ ምክንያት በወቅቱ ወይም ዘግይቶ፣ ውጫዊም ይሁን ውስጣዊ ተቆጥረው የማያልቁ አደገኛ መዘዞችን ስለሚያመጣ ነው። ቀጥለውም መልክተኛው -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: የሰው ልጅ የግድ መጥገብ አለብኝ ካለም የሚመገበውን ምግብ የሆዱ ሲሶውን ያህል ያድርግ። የተቀረውን ሲሶ ደግሞ ለመጠጡ ያድርገው። መጣበብና ጉዳት እንዳይደርስበት፣ አላህ ግዴታ ያደረገበትን የዲኑ ወይም የዱንያ ጉዳዩን ከመፈፀም እንዳያሳንፈው ሲል ሲሶውን ደግሞ ለትንፋሹ ያድርግለት።

فوائد الحديث

አመጋገብንና አጠጣጥን አለማብዛት ይገባል። ጥጋብ ማብዛት በሽታና ህመሞችን የሚያስከትል ከመሆኑ አንፃር ይህ ሐዲሥ ሁሉንም የህክምና መሰረቶች የሚጠቀልል መሰረት የሆነ ሐዲሥ ነው።

የመመገብ ኣላማው ጤንነትንና ሀይልን መጠበቅ ነው። ጤንነትና ሀይል ሲኖር ሰላማዊ ህይወት ይኖራል።

ሆድን በምግብ በመሙላት አካልም ላይ ሆነ ዲን ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች አሉ። ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል: "ጠግቦ ከመብላት አደራችሁን ተጠንቀቁ። እጅግ ጠግቦ መብላት ሰውነትን የሚያበላሽና ከሶላትም የሚያሳንፍ ነው።"

አመጋገብ ከብይን አንፃር ሲታይ የተለያዩ ክፍሎች ይኖሩታል: ግዴታ የሆነ አመጋገብ: ይህም ህይወትን ለማቆየትና ባለመመገቡ ወደ ጉዳት የሚያደርስ ምግብ ነው። የሚፈቀድ የሆነ አመጋገብ: ይህም የግድ መብላት ካለበት መጠን የጨመረና ጉዳት ያደርሳል ተብሎ የማይሰጋ አመጋገብ ነው። የሚጠላ የሆነ አመጋገብ: ይህም ጉዳት ያደርሳል ተብሎ የሚያሰጋ ምግብ ነው። ክልክል የሆነ አመጋገብ: ይህም ጉዳት እንደሚያደርስ የታወቀ አመጋገብ ነው። የሚወደድ የሆነ አመጋገብ: ይህም አላህን በማምለክ ላይ ለመታገዝ ተብሎ የሚመገቡት አመጋገብ ነው። ይህንንም በሐዲሡ ውስጥ በሶስት ደረጃዎች ተጠቃለው እናገኛቸዋለን። የመጀመሪያው: ሆድን መሙላት ነው። ሁለተኛው: ጀርባውን የሚያቆምለት ያህል ጉርሻዎች ናቸው። ሶስተኛው: "ሲሶውን ለምግቡ፣ ሲሶውን ለመጠጡ፣ ሲሶውን ለትንፋሹ ያድርግ።" ያሉት ነው። ይህ ሁሉ ግን የሚመገበው ምግቡ ሐላል ከሆነ ነው።

ይህ ሐዲሥ ከህክምና መርሆዎች መካከል አንዱ መርህ ነው። የህክምና እውቀት የሚሽከረከረው በሶስት መሰረቶች ላይ ነው። ሀይልን መጠበቅ፣ ምግብን ማሳነስና አቅምን መጠቀም ላይ ነው። ይህ ሐዲሥ ሁለቱን የመጀመሪያዎቹን ጠቅሷቸዋል። አላህም እንዲህ ብሏል: {ብሉም ጠጡም አታባክኑም። እርሱ አባካኞችን አይወድምና።} [አልአዕራፍ: 31]

እስልምና የሰው ልጅ ለዲኑም ሆነ ለዱንያው የሚጠቅመውን ማካተቱ የዚህ ሸሪዓን ሙሉነት ያስረዳናል።

ሸሪዓ ካካተታቸው እውቀቶች መካከል የህክምና መሰረቶችና የህክምና አሰጣጥ አይነቶች አንዱ ነው። በሸሪዓ ስለማርና ጥቁር አዝሙድ የመጣውም ይህን ያመሳክርልናል።

የሸሪዓ ህግጋቶች ጥበብን ያጠቃለሉ መሆናቸውን እንረዳለን። የሸሪዓ ህግጋቶች ጉዳትን በመከላከልና ጥቅምን በማምጣት ላይ የተገነቡ ናቸው።

التصنيفات

ከዝንባሌና ስሜት ማውገዝ