አንዳችሁ ወደ መቀመጫ ስፍራ የደረሰ ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ፤ ከመቀመጫ ስፍራ መነሳት የፈለገም ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ። መጀመሪያ ያቀረበው ሰላምታ መጨረሻ ላይ ከሚያቀርበው ሰላምታ…

አንዳችሁ ወደ መቀመጫ ስፍራ የደረሰ ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ፤ ከመቀመጫ ስፍራ መነሳት የፈለገም ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ። መጀመሪያ ያቀረበው ሰላምታ መጨረሻ ላይ ከሚያቀርበው ሰላምታ የበለጠ አይደለም።

ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፡ "አንዳችሁ ወደ መቀመጫ ስፍራ የደረሰ ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ፤ ከመቀመጫ ስፍራ መነሳት የፈለገም ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ። መጀመሪያ ያቀረበው ሰላምታ መጨረሻ ላይ ከሚያቀርበው ሰላምታ የበለጠ አይደለም።"

[ሐሰን ነው።] [An-Nasaa’i]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰዎች ወደ ተቀማመጡበት ስፍራ የመጣ ሰው ሰላምታ እንዲያቀርብና መነሳትም የፈለገ ጊዜ የተቀማመጡትን ሰዎች በድጋሚ ሰላምታ እንዲያቀርብላቸው ጠቆሙ። በሚመጣበት ወቅት (ሲቀላቀላቸው) ያቀረበው የመጀመሪያው ሰላምታ በሚለያይበት ወቅት (ሲሰናበታቸው) ከሚያቀርበው የመጨረሻ ሰላምታ የበለጠ የሚያደርገው ነገር እንደሌለ ተናገሩ።

فوائد الحديث

ሰላምታን በማሰራጨት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

በምንገናኝበትም ሆነ በምንለያይበት ወቅት የተቀማመጥናቸው ሰዎች ላይ ሰላምታ በማቅረብ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(… መነሳት በፈለገ ጊዜ …) ማለታቸው ከተቀመጠበት ስፍራ ማለታቸው ነው። (… የመጀመሪያው ሰላምታ የተሻለ አይደለም።) ማለታቸው ሁለቱንም ባጠቃላይ መተግበር የተረጋገጠ ሱና ነው። የመጀመሪያውን ከመፈፀም ጋር ሁለተኛው የሚተውበት ምንም ምክንያት የለም ለማለት ነው።"

التصنيفات

የሰላምታና የማስፈቀድ ስነ-ስርዓት