የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱጁድ ውስጥ እንዲህ ይሉ ነበር "አላሁመግፊርሊ ዘንቢ ኩለሁ ዲቀሁ ወጂለሁ፣ ወአወለሁ ወአኺረሁ፣ ወዐላኒየተሁ ወሲረሁ"»…

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱጁድ ውስጥ እንዲህ ይሉ ነበር "አላሁመግፊርሊ ዘንቢ ኩለሁ ዲቀሁ ወጂለሁ፣ ወአወለሁ ወአኺረሁ፣ ወዐላኒየተሁ ወሲረሁ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ደቂቁንም ትልቁንም፣ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም፣ ግልፁንም፣ ድብቁንም ወንጀሌን ሁሉንም ማረኝ።

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱጁድ ውስጥ እንዲህ ይሉ ነበር "አላሁመግፊርሊ ዘንቢ ኩለሁ ዲቀሁ ወጂለሁ፣ ወአወለሁ ወአኺረሁ፣ ወዐላኒየተሁ ወሲረሁ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ደቂቁንም ትልቁንም፣ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም፣ ግልፁንም፣ ድብቁንም ወንጀሌን ሁሉንም ማረኝ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሱጁዳቸው ወቅት እንዲህ እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር: "አላህ ሆይ ወንጀሌን ማረኝ" በመሸሸጊያህ ሸሽገኝ፤ ተከትሎት የሚመጣውን መከራንም ጠብቀኝ፤ ይቅር በለኝ፤ እለፈኝ (ሁሉንም) ማለትም (ደቂቁንም) ትንሹንም ጥቃቅኑንም፤ (ትልቁንም) ግዙፉንም ብዙውንም፤ (የመጀመሪያውንም) የመጀመሪያውን ወንጀሌንም፤ (የመጨረሻውንም) በነርሱ መካከል ያለውን ወንጀሌንም (ግልፁንም ድብቁንም) ከአንተ በቀር ማንም የማያውቀውን ወንጀሌንም ማረኝ።

فوائد الحديث

ኢብኑል ቀይዪም እንዲህ ብለዋል "ትናንሽንም፣ ትላልቅንም፣ ደቂቁንም፣ ግዙፉንም፣ የመጀመሪያውንም፣ የመጨረሻውንም፣ ድብቁንም፣ ግልፁንም ወንጀሎች ብሎ በዚህ በሚጠቀልልና በሚሰበስብ መልኩ ምህረት እንዲያገኝ መለመን ባሪያው ላወቀውም ሆነ ላላወቀው ወንጀሉ ሁሉ ተውበት እንዲያደርግ ነው።"

(ደቂቁንም) የሚለውን (ትልቁንም) ከሚለው ያስቀደሙት ጠያቂው ጥያቄውን ቀስ በቀስ እንዲወጣና እንዲያሳድግ ነው። ሌላው ምክንያትም ብዙ ጊዜ ትላልቅ ወንጀሎች የሚከሰቱት በትናንሽ ወንጀሎች ላይ በመዘውተርና ትኩረት ባለመስጠት ነው። ትናንሽ ወንጀሎች ወደ ትላልቅ ወንጀሎች ያደርሳሉ። ወደ አንድ ነገር የሚያደርሱ ነገሮች ደግሞ በማፅደቅም ይሁን በማስወገድ ረገድ መቀደማቸው የተገባ ነው።

ከትናንሹም ከትላልቁም ከሁሉም ወንጀሎች ምህረትን በመፈለግ ወደ አላህ መዋደቅ ተገቢ ነው።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ዱዓ ስናደርግ ማጠንከርና አንዱ ቃል ከአንዱ ቃል ቢያብቃቃን እንኳ ቃላቶችን ማብዛት እንደሚገባ ያስረዳናል።

التصنيفات

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚክር ዙሪያ ያላቸው መመሪያ