የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ እስኪ ንገሩኝ ምን ላድርግ?

የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ እስኪ ንገሩኝ ምን ላድርግ?

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «አንድ ሰውዬ ወደ አላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ እስኪ ንገሩኝ ምን ላድርግ?" እርሳቸውም "ገንዘብህን እንዳትሰጠው" አሉት። እርሱም "ከተጋደለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተም ተጋደለው።" አሉት። እርሱም "ቢገለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተ ሰማዕት ነህ።" አሉት። እርሱም "ብገለውስ?" አላቸው። እርሳቸውም "እርሱ እሳት ውስጥ ነው።" አሉት።»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እስኪ ንገሩኝ?" እርሳቸውም "ገንዘብህን መስጠት አይጠበቅብህም" አሉት። እርሱም "ከተጋደለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተም ተጋደለው።" አሉት። እርሱም "እርሱ ቢገለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተ ሰማዕት ነህ።" አሉት። እርሱም "እኔ ብገለውስ?" አላቸው። እርሳቸውም "እርሱ የትንሳኤ ቀን በእሳት ውስጥ ለመቀጣት የተገባ ነው።" አሉት።

فوائد الحديث

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ለቤተሰብ (ክብር) መከላከል ያለምንም ልዩነት ግዴታ ነው። የራስን ነፍስ ለመከላከል ብሎ በመግደል ዙሪያ ግን በኛም ይሁን በሌሎች መዝሀብ ውስጥ ልዩነት አለው። ለገንዘብ መከላከል ግዴታ ሳይሆን ፍቁድ የሆነ ነገር ነው።"

ይህ ሐዲሥ ከተግባር በፊት እውቀት እንደሚቀደም ይጠቁማል። ይኸውም ይህ ሶሓባ የአላህን መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከመተግበሩ በፊት ያለበትን ግዴታ መጠየቁ ነው።

ግፈኛን ለመከላከል በምንወስደው እርምጃ ከታች ወደ ላይ በቅደም ተከተል መሆን ይገባዋል። መጋደል ከመጀመር በፊት በምክር ወይም የይድረሱልኝ ጥሪ በማሰማት ይጀምራል። ወደ መጋደል ሲገባም አላማው ራስን መከላከልን አስቦ እንጂ መግደልን አስቦ መሆን የለበትም።

የሙስሊም ደሙ፣ ገንዘቡና ክብሩ እርም ነው።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ሰማዕትነት ሶስት ክፍል እንዳለው እወቅ! የመጀመሪያው: በትክክለኛ መንስኤ ከሃዲያንን ሲዋጋ በጦርነቱ ምክንያት የሞተ ነው። ይህ በመጪው አለምም ምንዳ በዱንያም ህግጋት የሰማዕቶችን ብይን ነው የሚይዘው። እርሱም አይታጠብምም አይሰገድበትምም። ሁለተኛው: በዱንያዊው ህግጋት ሳይሆን በምንዳ ሰማዕትነትን ያገኘ ነው። እርሱም በሆድ ህመም የሞተ፣ በወረርሽኝ የሞተ፣ ተንዶበት የሞተ፣ ለገንዘቡ ሲከላከል የሞተና ሌሎችም ሶሒሕ ሐዲሦች ውስጥ ሰማዕት ተብለው የተጠቀሱ እዚህ ውስጥ ይካተታሉ። ይህ ይታጠባል ይሰገድበታልም። ለርሱ ግን በመጪው አለም የሰማዕቶች ምንዳ ይሰጠዋል። ይህ ሲባል ግን ከመጀመሪያዎቹ ጋር እኩል የሆነን ምንዳ ማግኘቱን አያስፈርድም። ሶስተኛው: ምርኮ የሰረቁና የመሳሰሉትን (ጥፋት የፈፀሙ)፤ ከከሃዲያን ጋር እየተዋጉ ቢሞቱም ሰማዕት እንደማይባሉ በሐዲሦች የተጠቀሱ ሰዎች ናቸው። እነዚህ አለማዊ የሰማዕት ህግጋት ተፈፃሚ ይሆንላቸዋል አይታጠቡም አይሰገድባቸውም። በመጪው አለም ግን የተሟላ ምንዳ የላቸውም።"

التصنيفات

ሸሪዓዊ አላማዎች, ወንጀለኞችን ማውገዝ