إعدادات العرض
ሱብሓነሏሂል ዐዚም ወቢሐምዲሂ ያለ ሰው ጀነት ውስጥ ለርሱ የተምር ዛፍ ይተከልለታል።
ሱብሓነሏሂል ዐዚም ወቢሐምዲሂ ያለ ሰው ጀነት ውስጥ ለርሱ የተምር ዛፍ ይተከልለታል።
ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሱብሓነሏሂል ዐዚም ወቢሐምዲሂ ያለ ሰው ጀነት ውስጥ ለርሱ የተምር ዛፍ ይተከልለታል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili සිංහල ไทยالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና (ሱብሓነሏሂ) አላህ ጥራት የተገባው ነው። (አልዐዚም) በዛቱ፣ በባህሪያቱና በድርጊቱ ታላቅ ነው። (ወቢሐምዲህ) የምሉዕነት መገለጫዎቹን ማስጠጋት አቆራኝቼ አጠራዋለሁ ያለ ሰው ይህቺን ውዳሴ ባለ ቁጥር በጀነት መሬት ላይ የተምር ዛፍ ይተከልለታል አሉ።فوائد الحديث
አላህን ማውሳት በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ከነዚህም ዚክሮች መካከል ከማመስገን ጋር ማጥራት አንዱ ነው።
ጀነት ሰፊ ናት። የጀነት ተክሎችም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ)ና ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ናቸው። ይህም በአላህ ፀጋና ችሮታ ነው።
ሐዲሡ ውስጥ ከሌሎች ዛፎች ተለይቶ የተምር ዛፍ የተጠቀሰው ጥቅሙ የበዛና ፍሬው ጣፋጭ ስለሆነ ነው። ስለዚህም አላህ ቁርአን ውስጥ አማኞች በእምነታቸው ላይ ያላቸውን ምሳሌ በተምር ዛፍ ነው የመሰለው።
التصنيفات
አላህን የማውሳት ጥቅሞች