إعدادات العرض
አልላሁመ ቂኒ ዐዛበከ የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ባሮችህን በምትሰበስብበት ወይም በምትቀሰቅስበት ቀን ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ማለት ነው።
አልላሁመ ቂኒ ዐዛበከ የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ባሮችህን በምትሰበስብበት ወይም በምትቀሰቅስበት ቀን ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ማለት ነው።
ሑዘይፋህ ቢን አል'የማን -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንዳስተላለፉት: «ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መተኛት የፈለጉ ጊዜ እጃቸውን ጭንቅላታቸው ስር ያኖሩ ነበር። ቀጥለውም እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ቂኒ ዐዛበከ የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ባሮችህን በምትሰበስብበት ወይም በምትቀሰቅስበት ቀን ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ማለት ነው።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული සිංහල Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለመተኛት ስፍራቸውን ሲይዙ ቀኝ እጃቸውን ይንተራሱና ቀኝ ጉንጫቸውን ቀኝ እጃቸው ላይ በማኖር እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ቂኒ ዐዛበክ" አላህ ሆይ! ጌታዬ ቅጣትህን ጠብቀኝ። "የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ" የሒሳብ ቀን የትንሳኤ ቀን ማለት ነው።فوائد الحديث
የዚህ የተባረከ ዱዓ ደረጃንና ነቢዩን -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመከተል ይህንን አዘውትሮ ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
በቀኝ ጎን መተኛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "አላህ ሆይ ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ከሚለው ንግግር የምንወስደው ትምህርት አስተዋይ የሆነ ሰው እንቅልፍን ሞትንና ከሞት በኋላ ያለውን መቀስቀስ ለማስታወሻነት ሊገለገልበት እንደሚገባ ነው።
የትንሳኤ ቀን ከአላህ ቅጣት መጠበቅ የሚገኘው በአላህ ችሮታና እዝነት ለመልካም ስራ በመገጠሙና አላህ ወንጀሉን በመማሩ ነው።
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለጌታቸውና ረዳታቸው ለአላህ የነበራቸውን መተናነስ እንመለከታለን።
በሐዲሡ ውስጥ (በቂያማ ቀን) መሰብሰብና መመለስ ተረጋግጧል። ሰዎች ወደ ጌታቸው በስራቸው ሊተሳሰባቸው ይመለሳሉ። መልካምን ያገኘ ሰው አላህን ያመስግን ከዛ ውጪ ያገኘ ሰው ግን ከነፍሱ ውጪ ማንንም አይውቀስ። ይህቺ በምድር የሚሰሯት ስራቸውን ነው አላህ ለነርሱ ጠብቆ የሚያቆይላቸው።
ሶሓቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ነቢዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በእንቅልፋቸው ወቅት የነበራቸውን ሁኔታ እንኳ ሳይቀር ለመግለፅ እንደጣሩ እንረዳለን።
"ቀኝ እጃቸውን ከጉንጫቸው ስር አኖሩ።" ከሚለው ንግግርም እንደምንረዳው ማስረጃ በተቃራኒ መጠቀማቸውን ካስረዳው ውጪ የነቢዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተለምዷቸው በሁሉም ነገር ቀኝን እንደሚያስቀድሙ ነው።
በቀኝ ጎን እንቅልፍ መተኛት በዛ ሁኔታ ሲተኛ ቀልብ ስለማትረጋጋ ቶሎ ለመንቃት ያግዛል። ቀልብ ምቾት ኑሯት የምታርፈው በግራ አቅጣጫ ስትሆን ነው። ሰውዬው በግራ አቅጣጫ ሲተኛ ውስጣዊ አካላቱ ቀልቡ ላይ ስለምትደገፍ (ስለሚዘነበል) ቀልቡ ትጎዳለች።
التصنيفات
የእንቅልፍና የመንቃት ስነ-ስርዓት