إعدادات العرض
ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል የባህሩን ውሃ የምታበላሽ የሆነችን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት።
ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል የባህሩን ውሃ የምታበላሽ የሆነችን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለሰፊያ (ነውር’ኮ) እንዲህ እንዲህ ነገሯ ራሱ ይበቃሃል። አልኳቸው። (አንዱ የሐዲሥ ዘጋቢ እንዲህ እንዲህ ነገሯ ይበቃሃል በማለት የፈለገችው እጥረቷን ነው ብለዋል።) እርሳቸውም "ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል የባህሩን ውሃ የምታበላሽ የሆነችን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት። "እንዲህም አለች "ለርሳቸው የሆነ ሰው የሚያደርገውን አስመስዬ በድርጊት አሳየኃቸው።" እርሳቸውም "ለኔ እንዲህ እንዲህ ቢሰጠኝ እንኳ ሰውን ማስመሰል አያስደስተኝም (አልወድም)።" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog Kurdî Русский Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili Hausa සිංහල ไทยالشرح
የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ከሶፊያ‘ኮ (የፈለገችውም የአማኞች እናትን ነው) ከአካላዊ ነውሮቿ እርሷ አጭር መሆኗ ይበቃሃል።" አለቻቸው። እርሳቸውም "ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል ውሃውን አሸንፋ የምትለውጠውንና የምታበላሸውን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት። እንዲህም አለች "የሆነን ሰው ዝቅ በማድረግ መልኩ የሚሰራውን ስራ አምሳያ አስመስዬ ሰራሁላቸው።" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ነውሩን መናገር ወይም የሚሰራውን ስራ አስመስዬ በመስራቴ ወይም የሚናገረውን አምሳያ በመናገሬ ለዚህ ተግባር ከዱንያ እጅግ በርካታ ነገር ቢሰጠኝ ራሱ ማድረጉ አያስደስተኝም።" አሉ።فوائد الحديث
ከሀሜት መከልከሉና መስፈራራቱን ተረድተናል።
በማሳነስና ዝቅ በማድረግ መልኩ ሰዎችን ማስመሰልና የነርሱን ሁኔታ መከተል ከተከለከለው ሀሜት ይመደባል።
አካላዊ ነውሮችን መግለፅ የሀሜት አንድ ክፍል ነው።
ቃዲ እንዲህ ብለዋል: «"መዝጅ" ማለት ሌላን ነገር ወደርሱ መቀላቀል፣ መለወጥ ማለት ነው። ሀሳቡም ይህ ሀሜት ባህር ውስጥ የሚቀላቀል ቢሆን ኖሮ የባህሩ ውሃ ከመብዛቱም ጋር ውሃውን ይለውጠው ነበር ማለት ነው። ጥቂት ተግባራት ቢቀላቀልበትስ ምን ሊሆን ይችል?»
በሚስቶች መካከል የሚከሰት ቅናት መጠቀሱን እንመለከታለን።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ውግዝ ተግባርን አለማፅደቃቸው።
ዱንያና ውስጧ ያሉ ነገሮች ከአላህ ውዴታና ከአላህ አለመቆጣት ጋር ሲነፃፀሩ ያነሱ መሆናቸውን እንረዳለን።
እስልምና ክብሮች በንግግርም ሆነ በተግባር እንዳይደፈሩ በመከልከል ክብር እንዲጠበቅ ያዘዘ የመልካም ስነምግባር ሃይማኖት ነው። ምክንያቱም ክብርን መንካት በሙስሊሞች መካከል ጠላትነትንና ጥላቻን የሚፈጥር ነውና።
التصنيفات
ውግዝ ስነ-ምግባር