ሰሌን ላይ የሚተኛ ሰው ቆዳው ላይ ሰንበር እንደሚያወጣው ፈተናም በቀልብ ላይ በተደጋጋሚ ትቀርባለች።

ሰሌን ላይ የሚተኛ ሰው ቆዳው ላይ ሰንበር እንደሚያወጣው ፈተናም በቀልብ ላይ በተደጋጋሚ ትቀርባለች።

ከሑዘይፋህ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘንድ ነበርን እንዲህም አለን: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለ ፈተና ሲያወሱ የሰማ ማንኛችሁ ነው?" የተወሰኑ ሰዎችም "እኛ ሰምተናቸዋል።" አሉ። ዑመርም "ምናልባት ሰማን የምትሉት ሰውዬው በቤተሰቡና በጎረቤቶቹ የሚፈተነውን አይነት ፈተና ይሆን?" አላቸው። እነርሱም "አዎ" አሉ። ዑመርም "ይህማ ሶላት፣ ፆምና ሶደቃ ያስምረዋል። ነገር ግን ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደ ባህር ነውጥ ስለምትናወጠው ፈተና ሲያወሱ የሰማ ማንኛችሁ ነው?" አለ።» ሑዘይፋህ እንዲህ አለ: «ዑመር ሰዎችን ዝም አስባለ። እኔም: እኔ ሰምቻለሁ። አልኩኝ። ዑመርም "አላህ አባትህ ምን አይነት ልጅ እንዲወልድ ነው ያደረገልን! አንተ ሰምተሃልን?" አለ።» ሑዘይፋም እንዲህ አለ «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:- "ሰሌን ላይ የሚተኛ ሰው ቆዳው ላይ ሰንበር እንደሚያወጣው ፈተናም በቀልብ ላይ በተደጋጋሚ ትቀርባለች። ፈተናዋ ወደ ውስጡ የገባችበት ማንኛውም ቀልብ ጥቁር ጠብታ ቀልቡ ላይ ታርፋለች። ፈተናዋን ያወገዘ ማንኛውም ቀልብ ደሞ ነጭ ጠብታ ቀልቡ ላይ ታርፋለች። ይህም ሁለት ቀልብ እስኪሆን ድረስ ነው። ሰማይና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ ፈተና የማይጎዳት እንደ ለስላሳ ድንጋይ የነጣ ቀልብ እና ሌላኛው ደግሞ እንደተገለበጠ ኩባያ ከስሜቱ ጋር የተስማማውን ካልሆነ በቀር ጥሩን ጥሩ የማይል መጥፎንም የማያወግዝ ጥቁር ሆኖ አመዳም ቀለም የያዘ ቀልብ ናቸው።"» ሑዘይፋ እንዲህም አለ፡ «ለዑመር በአንተ እና በፈተናዋ መካከል የተዘጋ በር አለ። ልትሰበርም ትቀርባለች ብዬ ነገርኩት። ዑመርም "አላህ ያጠንክርህና ይሰበራል ማለት ነው? ቢከፈትስ ድጋሚ ሊዘጋ ይችላልን?" አለ። እኔም አይ እንደውም ይሰበራል። ንግግሬ ምንም ስህተት የሌለው መሆኑንና ያ በር ማለት የአንድ ሰውዬ መገደል ወይም መሞት እንደሆነ አስረግጬ ነገርኩት።» አቡ ኻሊድ እንዲህ አለ: «ለሰዕድ እንዲህ አልኩት "የጠቆረ አመዳም ቀለም ማለት ምን ማለት ነው?" ሰዕድም "ከጥቁረት ጋር የተቀላቀለ ንጣት ነው።" አለኝ። "የተዘነበለ ባልዲ ማለትስ" አልኩት። እርሱም "የተገለበጠ ማለት ነው።" አለኝ።»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች መሪ ዑመር ቢን ኸጧብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከተወሰኑ ሶሓቦች ጋር ተቀምጦ ሳለ ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለ ፈተና ሲያወሱ የሰማ ማንኛችሁ ነው?" አንዳንዶቹም "እኛ ስለፈተና ሲያወሱ ሰምተናቸዋል።" አሉ። ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁ "ምንአልባት የሰማችሁት ሰውዬው በግል ህይወቱ ዙሪያ በሚስቱና በልጆቹ ላይ ባለው ወሰን ያለፈ ውዴታው፤ ለነርሱ ባለው ስስት፣ ብዙ መልካም ነገር ትቶ በነርሱ በመጠመድ ወይም ለነርሱ ማሟላት ያለበትን ሐቅ ባለማሟላት፤ ስርዓት ከማስያዝና ከማስተማር ቸልተኛ በመሆን የሚፈተነውን ፈተናና ልክ እንደዚሁ ሰውዬው በጎረቤቱና በመሳሰሉት የሚፈተነውን ፈተና ነው። ይህንን ነው አይደል ሰምተናል ያላችሁት?" አላቸው። እነርሱም "አዎ" አሉ። ዑመርም "ይህ ፈተናማ የሚያስፈርደው አላህን መተሳሰብ ነው። ከነዚህ መካከል እንደሶላት፣ ፆምና ሶደቃ ባሉ መልካም ስራዎችም ሊማሩ የሚችሉ ወንጀሎች አሉ።" አለ። "ነገር ግን ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አጠቃላይ ስለሆነው፣ ግዝፈቱ ከፍተኛ ስለሆነና ስርጭቱ በብዛት ስለሚዳረስ ባህር እንደሚናወጠው ሰዎችን ስለሚያናውጠው ፈተና ሲያወሩ ማንኛችሁ ነው የሰማው?" አለ። ሰዎችም ዝም አሉ። ሑዘይፋህ ቢን የማንም ረዲየሏሁ ዐንሁ "እኔ ሰምቻለሁ።" አለ። ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁ ተደሰተ። ለርሱም "አላህ አባትህ ምን አይነት ልጅ እንዲወልድ ነው ያደረገልን! እስኪ ንገረን።" አለው። ሐዘይፋም እንዲህ አለ "ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "የተኛ ሰው ጎን ላይ የሰሌን ምንጣፍ እንደሚለጠፈው ፈተናም በሰው ቀልብ ላይ ትለጠፋለችም ግልፅ ትሆናለችም። ፈተናዋ በቀልብ ላይ ከመለጠፏ የተነሳም ቀልቡ ላይ ምልክት ታወጣበታለች። ይህቺ ፈተናም በተደጋጋሚ ተመላልሳ ትከሰታለች። ይህቺ ፈተና የገባችበት፣ የወደዳት፣ መጠጥ ወደ ሰውነት ውስጥ እንደምትቀላቀለው ከቀልቡ ጋር የተቀላቀለችበት ማንኛውም ቀልብ በቀልቡ ላይ ጥቁር ጠብታ ታርፋለች። ይህቺን ፈተና ያልተቀበለ ማንኛውም ቀልብ በቀልቡ ላይ ነጭ ጠብታ ታርፋለች። በዚህም ቀልቦች ሁለት አይነት ይሆናሉ። አንደኛው: በኢማን ላይ ያለው ጥንካሬ ከፍተኛ ስለሆነ፣ ከጉድለት የፀዳ ስለሆነ ፈተናዋ ያልተለጠፈችበትና ምልክት ያላሳረፈችበት ነጭ ቀልብ ነው። የርሱ ቀልብ ምሳሌም ምንም ነገር እንደማይይዝ ለስላሳ አልማዝ ነው። አላህን እስኪገናኝ ድረስም ምንም ነገር አይጎዳውም። ሌላኛው ቀልብ ደግሞ በፈተናው ሰበብ ቀለሙ ወደ ጥቁርነት የተለወጠና ውሃ እንደማይገባበት የተገለበጠ ጆክ የመሰለ ቀልብ ነው። ልክ እንደዚሁ ይህ የጠቆረ ቀልብ መልካምና ጥበብ የማይቀርበው፤ እንዲሁም የወደደውና ለስሜቱ የተመቸው ካልሆነ በቀር መልካሙን መልካም የማይልና መጥፎን የማያወግዝ ቀልብ ነው።" ሑዘይፋም ለዑመር እንዲህ አለው: "ይህ ፈተና አንተ በህይወት እያለህ አይከሰትም። በአንተና በዚህች ፈተና መካከል ሊሰበር የቀረበ የተዘጋ በር አለ።" ዑመርም "ይሰበራልን? ቢከፈትስ ተመልሶ ሊዘጋ ይችላልን?" አለ። ሑዘይፋም "በፍፁም! ይልቁንም ይሰበራል። ይህ በርም የሆነ ሰው መገደሉ ወይም መሞቱ ነው።" አለ። ሑዘይፋ እንዲህም አለ "አሁን ያወራሁት የተረጋገጠ እውነተኛ ወሬ ነው። የፀሃፊዎች ዘገባም የአንድ ሰው የምርምር ሀሳብ ውጤትም አይደለም። ይልቁንም የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሐዲሥ ነው።"

فوائد الحديث

አጠቃላይ የሆነ ፈተና የደም መፋሰስ፣ የገንዘብ ውድመትና የሰላም መጥፋትን ስለሚያስከትል አደገኛ መሆኑን እንረዳለን።

ግለሰባዊ የሆኑ ፈተናዎች ከእምነት ጋር ተያያዥ ከሆኑ ሰውዬው የተወገዘ ይሆናል። ምክንያቱም ግለሰባዊ ፈተናዎች ወይ በቢድዓ ወይ በወንጀል የሚመጡ ናቸውና። ከዱንያ ጋር ተያያዥ ከሆኑ ደግሞ ለሰውዬው ፈተናና ሙከራ ነው። ከርሱ የሚጠበቀውም ትእግስት ማድረግ ነው።

ቀልብ በሚያገኘው ፈተና ምክንያት ተፅእኖ እንደሚደርስበት እንረዳለን። የተገጠመ ሰው የሚባለው አላህ በቀና መንገድ ላይ ለፅናት የመራው ሰው ነው።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «የተሕሪር ፀሐፊ እንዲህ ብለዋል: "የሐዲሡ ሃሳብ: አንድ ሰው ስሜቱን የተከተለና ወንጀልን የፈፀመ ጊዜ በሁሉም የሚፈፅማቸው ወንጀሎች ልክ ወደ ቀልቡ ፅልመት ይገባል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ይፈተናልም የእስልምና ብርሃንም ከርሱ ላይ ይጠፋል። ቀልብ እንደ ኩባያ ናት። የተገለበጠ ጊዜ ውስጡ ያለውም ይደፋል፤ ከዛ በኋላ ወደርሱ የሚገባ ነገርም አይኖርም።"

ዑመር ለሑዘይፋ "አባት አይኑርህና" ማለታቸው ትርጉሙ "በዚህ ጉዳይ አስተውል ተጠንቀቅ! አጋዥ የሌለው ሰው እንደሚጠነቀቀው ተጠንቀቅ! ለማለት ነው።

የዑመርን ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ደረጀ እንረዳለን። ዑመር በሰዎችና በፈተና መካከል የተዘጋው በር ነው።

التصنيفات

ከዝንባሌና ስሜት ማውገዝ