إعدادات العرض
ወደ ሰማይ እንዳርግ በተደረግኩበት ወቅት የነሃስ ጥፍር ባላቸውና በነዛም ጥፍሮች ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን በሚቧጭሩ ሰዎች በኩል አለፍኩ።
ወደ ሰማይ እንዳርግ በተደረግኩበት ወቅት የነሃስ ጥፍር ባላቸውና በነዛም ጥፍሮች ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን በሚቧጭሩ ሰዎች በኩል አለፍኩ።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ «ወደ ሰማይ እንዳርግ በተደረግኩበት ወቅት የነሃስ ጥፍር ባላቸውና በነዛም ጥፍሮች ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን በሚቧጭሩ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም "ጂብሪል ሆይ! እነዚህ እነማን ናቸው?" ብዬ ጠየቅኩት። እርሱም "እነዚህ የሰዎችን ስጋ የሚበሉና የሰዎችን ክብር የሚያጎድፉ ናቸው።" በማለት መለሰልኝ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Русский Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - በኢስራእና ሚዕራጅ ምሽት ወደ ሰማይ በወጡበት ወቅት የነሃስ ጥፍሮች ባሏቸውና ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውንም በሚቧጭሩና በሚቦጭቁ ሰዎች በኩል እንዳለፉ ተናገሩ። ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎች በዚህ ቅጣት እንዲመነዱ ያደረጋቸው ምንድነው? ብለው ጠየቁት። ጂብሪልም ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎችን የሚያሙና ያለአግባብ ስለሰዎች ክብር የሚናገሩ ናቸው። ብሎ መለሰላቸው።فوائد الحديث
ሃሜትን በማስመልከት ከባድ ማስጠንቀቂያ መምጣቱንና የሚያማ ሰው የሰውን ስጋ ከመብላት ጋር እንደተመሳሰለ እንረዳለን።
በሃሜትና በመሳሰሉት የሰዎችን ክብር መንካት ከትላልቅ ወንጀሎች እንደሆነ እንረዳለን።
ጢቢይ "የሚቧጭሩ" በሚለው የሐዲሡ ቃል ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "ፊትንና ደረትን መቧጨር የሙሾ አውራጅ ሴቶች ባህሪ ከመሆኑ አንፃር የሙስሊሞችን ክብር ለሚያጎድፉ ሰዎችም መቀጫቸው ያንኑ ባህሪ መላበስ አደረገው። ይህም ሁለቱም ባህሪያት የወንዶች ሳይሆኑ የሴቶች ለዛውም በአስቀያሚ ሁኔታና በመጥፎ ገፅታ ላይ ሲሆኑ የሚላበሱት ባህሪ እንደሆነ የሚገልፅ ነው።"
በሩቅ እውቀትና አላህና መልክተኛው - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - በተናገሩት ባጠቃላይ ማመን ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።
التصنيفات
ወንጀለኞችን ማውገዝ