إعدادات العرض
ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።
ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።
ከአቡል ዓባስ ሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ብሰራው አላህም የሚወደኝ ሰዎችም የሚወዱኝ የሆነን ስራ ጠቁሙኝ!" እርሳቸውም: "ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።»
[قال النووي: حديث حسن] [رواه ابن ماجه وغيره بأسانيد حسنة]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල دری অসমীয়া پښتو O‘zbek Tiếng Việt Македонски Nederlands Kiswahili ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ తెలుగు ไทย Moore Magyar Azərbaycan ქართული ಕನ್ನಡ ગુજરાતી Українська Shqip Кыргызча Српски Kinyarwanda тоҷикӣ Wolof Čeština தமிழ் नेपाली മലയാളം kmr ms Deutsch Lietuviųالشرح
አንድ ሰውዬ ሲሰራው አላህም የሚወደው ሰዎችም የሚወዱት የሆነን ስራ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲጠቁሙት ጠየቀ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዱንያ ትርፍ የሆኑ እንደ አኺራም የማይጠቅሙ የሆኑ ነገሮችን በተውክና ዲንህ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉብህን ነገሮች የተውክ ጊዜ አላህ ይወድሃል። ሰዎች እጅ ያለን የዱንያ ጥቅም ችላ ያልክ ጊዜ ደሞ ሰዎች ይወዱሃል። ምክንያቱም ሰዎች በተፈጥሯቸው ንብረታቸውን ይወዷታልና በንብረታቸው የተጋፋቸውን ይጠሉታል። ንብረታቸውን የተወላቸውን ደግሞ ይወዱታል በማለት መለሱለት።فوائد الحديث
በዱንያ ውስጥ ዛሂድ የመሆን ትሩፋትን እንረዳለን። ዙህድ ማለት: ለመጪው አለም የማይጠቅምን ነገር መተው ማለት ነው።
የዙህድ ደረጃው ከወረዕ የበለጠ ነው። ወረዕ ማለት የሚጎዳን ነገር መተው ማለት ሲሆን ዙህድ ግን ለመጪው አለም የማይጠቅምን ነገር መተው ማለት ነው።
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ዱንያ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ናት። በሷ ጉዳይ የሚጋፋቸውን ሰው በተጋፋቸው መጠን እነርሱ ዘንድ የተጠላ ይሆናል። እነርሱንና የሚወዱትን የተወላቸው ሰው ደሞ በዛ ልክ በቀልባቸው ውስጥ ተወዳጅ ይሆናል።
التصنيفات
ዱንያን ቸል ማለት (ዙህድ)ና ጥንቁቅነት