إعدادات العرض
አላህ ሆይ! ከመጪው አለም ኑሮ ውጪ ኑሮ የለም። ለአንሷሮችና ሙሃጂሮች ማራቸው።
አላህ ሆይ! ከመጪው አለም ኑሮ ውጪ ኑሮ የለም። ለአንሷሮችና ሙሃጂሮች ማራቸው።
ከአነስ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ሆይ! ከመጪው አለም ኑሮ ውጪ ኑሮ የለም። ለአንሷሮችና ሙሃጂሮች ማራቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Kurdî தமிழ் Magyar ქართული Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Hausa Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እውነተኛ ኑሮ በመጪው አለም በአላህ ውዴታ፣ እዝነትና ጀነት ውስጥ ያለው ነው እንጂ ሌላ ትክክለኛ ኑሮ እንደሌለ ተናገሩ። የዱንያ ኑሮ ተወጋጅ ነው። የመጪው አለም ኑሮ ዘውታሪና ቀሪ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምህረትን፣ መከበርንና መልካምነትን ለእነዚያ ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እና ሙሃጂሮችን ላስጠጉትና ገንዘባቸውን ላካፈሉት አንሷሮች በተጨማሪ የአላህን ውዴታና ችሮታ ፈልገው ሃገራቸውንና ገንዘባቸውን ትተው ለተሰደዱት ዱዓ አደረጉላቸው።فوائد الحديث
ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለዱንያ የነበራቸው ቸልተኝነትንና ሙሉ ለሙሉ ወደ መጪው አለም ራሳቸውን ያዞሩ መሆኑን እንረዳለን።
ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠፊ ከሆነው የዱንያ ጥቅም ኡመታቸው ችላ እንዲል መጣራቸውን እንረዳለን።
ሙሃጂሮችና አንሷሮች ምህረት እንዲያገኙ በነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ የተደረገላቸው በመሆናቸው የነርሱ ማዕረግ ከፍታ ተገልፆ እንመለከታለን።
አንድ ሰው በሚያገኘው የዱንያ መጣቀሚያ መደሰት የለበትም። ዱንያ ውስጧ ካሉት መከራዎችም ጋር ለመጥፋት ቅርብ ናትና። የመርጋትና የመዘውተርያ አገር የመጪው አለም አገር ነው።
التصنيفات
ዱንያን ከመውደድ ማውገዝ