አንድ ሙስሊም ሴት የአንድ ምሽት መንገድ ከርሷ ጋር የዝምድና ባለቤት የሆነ ወንድ ከሌለ በቀር ልትጓዝ አልተፈቀደላትም።

አንድ ሙስሊም ሴት የአንድ ምሽት መንገድ ከርሷ ጋር የዝምድና ባለቤት የሆነ ወንድ ከሌለ በቀር ልትጓዝ አልተፈቀደላትም።

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሙስሊም ሴት የአንድ ምሽት መንገድ ከርሷ ጋር የዝምድና ባለቤት የሆነ ወንድ ከሌለ በቀር ልትጓዝ አልተፈቀደላትም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንዲት ሙስሊም ሴት ከርሷ ጋር ከቅርብ ዘመዶች መካከል አንድ ወንድ ከሌለ በቀር የአንድ ምሽት መንገድ መጓዟ ክልክል እንደሆነ ተናገሩ።

فوائد الحديث

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሴት ለሐጅና ዑምራ ጉዞ ወይም ከሺርክ ሃገር ለመውጣት ካልሆነ በቀር ያለቅርብ ዘመድ ጉዞ ማድረግ እንደማይፈቀድላት ዑለሞች የተስማሙበት ጉዳይ ነው። ከዑለሞች መካከል ይህንን ከሐጅ መስፈርቶች መካከል አንዱ ያደረጉም አሉ።"

የእስልምና ሸሪዓ የተሟላ እንደሆነና ሴትን ልጅ በመጠበቅና በመከላከል ረገድ ምን ያህል ጥረት ያደረገ እንደሆነ እንረዳለን።

በአላህና በመጨረሻው ቀን ማመን ለአላህ ሸሪዓ መተናነስ (መዋረድ) እና የተቀመጠልን ገደብ ላይ መቆምን ያስፈርዳል።

የሴት ልጅ ቅርብ ዘመድ ባሏ ወይም በዝምድና ወይም በጥቢ ወይም በአማችነት ምክንያት ከርሱ ጋር ጋብቻ ለዘላለም እርም የተደረገባት ወንድ ነው። ይህ ዘመዷ ሙስሊም መሆኑ፣ ለአቅመ አዳም የደረሰ፣ አይምሮ ጤነኛ፣ ታማኝ መሆኑም መስፈርት ነው። ከቅርብ ዘመድነቱ የተፈለገውም ሴቲቱን እንዲጠብቃት፣ እንዲከላከልላትና ጉዳዮቿንም እንዲፈፅምላት ነው።

በይሀቂይ ሴት ልጅ ከቅርብ ዘመዷ ጋር ካልሆነ በቀር በማትጓዝበት የጉዞ ርቀት ዙሪያ ስለመጡ ዘገባዎች እንዲህ ብለዋል: "ዋናው ፍሬ ሃሳብ ማንኛውም ጉዞ ተብሎ ከተጠራ መንገድ ሴት ልጅ የሶስት ቀን መንገድም ሆነ ወይም የሁለት ቀን ወይም የአንድ ቀን ወይም የተወሰነ ርቀት ይሁን ወይም ከዚህ ውጪም ቢሆን ከባሏ ጋር ወይም ከቅርብ ዘመዷ ጋር ሁና ካልሆነ በቀር መጓዝ ትከለከላለች። ይህም ቀደም ብሎ ከተጠቀሰው የሙስሊም ሐዲሥ መጨረሻ ላይ ከኢብኑ ዐባስ ከዘገቡት ጥቅል ሓዲሥ አንፃር ነው፡ {ሴት ልጅ ከቅርብ ዘመዷ ጋር ካልሆነ በቀር እንዳትጓዝ።} ይህ ሐዲሥም ጉዞ ተብሎ የሚጠራን መንገድ ሁሉ ያጠቃልላል።" (ንግግራቸው አበቃ)። የተለያየ የጊዜ ገደብን የሚጠቁም ሐዲሥ የመጣው እንደጠያቂው ሁኔታና ስፍራ ልክ ነው።

التصنيفات

የጉዞ ህግጋትና ስነ-ስርዓት, የዑምራ ግዴታዎች