ነጭ ልብስ ምርጡ ልብሳችሁ ነውና ከልብሶቻችሁ መካከል ነጩን ልብስን ልበሱ። ሟቾቻችሁንም በርሱ ከፍኑ።

ነጭ ልብስ ምርጡ ልብሳችሁ ነውና ከልብሶቻችሁ መካከል ነጩን ልብስን ልበሱ። ሟቾቻችሁንም በርሱ ከፍኑ።

ከኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "ነጭ ልብስ ምርጡ ልብሳችሁ ነውና ከልብሶቻችሁ መካከል ነጩን ልብስን ልበሱ። ሟቾቻችሁንም በርሱ ከፍኑ።"»

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ነጭ ልብስ ምርጥ ልብስ ስለሆነ ወንዶች ነጭ ልብስ እንዲለብሱና ሟቾቻቸውንም በነጭ ልብስ እንዲከፍኑ ጠቆሙ።

فوائد الحديث

ነጭ ልብስ መልበስ እንደሚወደድ እንረዳለን። ከነጭ ውጪ ያለ ልብስም ይፈቀዳል።

ሟችን በነጭ ከፈን መከፈን እንደሚወደድ እንረዳለን።

ሸውካኒይ እንዲህ ብለዋል: "ሐዲሡ ነጭ ልብስ መልበስና ሟችን በነጭ ከፈን መከፈን የተደነገገ እንደሆነ ይጠቁማል። ይህም ከሌሎች ቀለሞች የፀዳና ውብ ስለሆነ ነው። ከሌሎች ቀለሞች ውብ መሆኑ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው። ከሌሎች ቀለሞች የፀዳ መሆኑ ደግሞ በርሱ ላይ ትንሽ ነገር ቢያርፍበት እንኳ ግልፅ ብሎ ይታያልና። በነዚህ ምክንያቶችም ሌሎችን ቀለሞች ይበልጣል።"

التصنيفات

የአለባበስ ስነ-ስርዓት