ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።

ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምሉዕ ኢማን ያለው አማኝ ሰዎችን በዘራቸው የሚተች፣ ስድብና እርግማን የሚያበዛ፣ ሃፍረተ ቢስነትን የተላበሰ ፀያፍ ድርጊትና ንግግርን የሚያበዛ እንዳልሆነ ተናገሩ።

فوائد الحديث

በሸሪዓዊ ጥቅሶች ውስጥ ክልክል በመተግበር ወይም ግዴታን በመተው ካልሆነ በቀር ኢማን ውድቅ አይደረግም።

አካላትን በመጠበቅና ከመጥፎ ተግባራት በመታቀብ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በተለይ ምላስን።

ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: (እጅግ ተቺና እጅግ ተራጋሚ) በማለት ሁለቱ በተጋኖ ቃል መጠቀሳቸው ትችትና እርግማን የሚገባውን ሰው በትንሹ መተቸትና መርገም የኢማን ሰዎችን በኢማን ከመገለፅ እንደማያጎድልባቸው ያስረዳል።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር, የመናገርና የዝምታ ስነ-ስርዓት