إعدادات العرض
አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ)…
አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።
ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kurdî Português සිංහල Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Nederlandsالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስለአንዳንድ የጀነት ፀጋዎች ተናገሩ። ጀነት ውስጥ ለአማኞች ትልቅና ውስጡ ሰፊ የሆነ ከአንድ ውስጡ ባዶ ከሆነ ወጥ ሉል ድንኳን ተዘጋጅቶላቸዋል። ወደ ሰማይ አግድመቱና ርዝመቱ ስልሳ ማይል የሚሆን ነው። ከአራት ማዕዘን ጎኖቹ መካከል በየሁሉም ጎንና ጥግ ሚስቶች አሉት። አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር አይተያዩም። አማኙም በመካከላቸው ለግንኙነት ይዞራል።فوائد الحديث
የጀነት ሰዎች ፀጋ ትልቅ እንደሆነ መገለፁን እንረዳለን።
መልካም ስራ ለሚሰሩ ሰዎች አላህ ያዘጋጀላቸውን ፀጋ በመግለፅ መልካም ስራ በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
التصنيفات
የጀነትና እሳት ባህሪዎች