ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ ነበር…

ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ ነበር የሚመልሱት።

ከአቢ ዐብደላህ አልጀደሊይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአማኞች እናት ዓኢሻን (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስነምግባር ጠየቅኳት። እርሷም እንዲህ አለች: "ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ ነበር የሚመልሱት።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለነቢዩ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስነምግባር ተጠየቀች። እርሷም "በተፈጥሯቸው በንግግራቸውና በተግባራቸው ፀያፍ አልነበሩም፤ ፀያፍን ለመስራትም አይጣጣሩምም አያስቡምም ነበር፤ በገበያ ስፍራ ድምፃቸውን ከፍ የሚያደርጉና የሚጮኹም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ አይመልሱም ነበር፤ ነገር ግን በውስጣቸው ይቅር በማለትና በውጭ ደግሞ በማለፍና ችላ በማለት መጥፎን በጥሩ የሚመልሱ ነበሩ።" ብላ መለሰች።

فوائد الحديث

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የተላበሱት የላቀ ስነምግባር መገለፁ፤ ከውግዝ ስነምግባርም መራቅ እንደሚገባም እንረዳለን።

መልካም ስነምግባር በመፈፀም ላይና ከመጥፎ ስነምግባር በመራቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ፀያፍ ንግግርንም ይሁን ቆሻሻ ወሬን ማውራት መወገዙን እንረዳለን።

በሰዎች ላይ ድምፅን ከፍ ማድረግና በነርሱ ላይ መጮህ መወገዙን እንረዳለን።

መጥፎን ተግባር በመልካም፣ በይቅር ባይነትና አውቆ በማለፍ መመለስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር, የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይቅር ባይነት