إعدادات العرض
እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ለእንግዶቹ 'ጡባ' ይሰጣቸዋል (አለላቸው)።
እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ለእንግዶቹ 'ጡባ' ይሰጣቸዋል (አለላቸው)።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ለእንግዶቹ 'ጡባ' ይሰጣቸዋል (አለላቸው)።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስልምና በተወሰኑ ሰዎች፣ በአናሳ ተከታዮች እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም እስልምናን የሚተገብር በማነሱ ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ሃሴት፣ ያማረ ሁኔታና የአይን ማረፊያ ለእንግዶቹ አለላቸው አሉ።فوائد الحديث
እስልምና ከተሰራጨና ከታወቀ በኋላም እንግዳነቱ መልሶ እንደሚከሰትበት መናገራቸው፤
ይህ ሐዲሥ ከነቢይነት ምልክቶች መካከል አንዱ ምልክት ነው። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከርሳቸው በኋላ የሚከሰተውን ተናግረው እንደተናገሩት መከሰቱ ነው።
ሀገሩንና ዘመዶቹን ለእስልምና ብሎ የተወ ሰው ያለው ደረጃ መገለፁ፤ ለርሱም ጀነት ይሰጠዋል።
እንግዶች ማለት: ሰዎች በተበላሹ ጊዜ የተስተካከሉና ሰዎች ያበላሹትንም የሚያስተካክሉ ናቸው።
التصنيفات
የደጋጎች ሁኔታ