إعدادات العرض
እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ…
እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶስት አይነት ሰዎችን በውርደትና ክስረት አፍንጫቸው በአፈር እንዲታሽ ረገሟቸው: የመጀመሪያው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱ ዘንድ ተወስተው በርሳቸው ላይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወይም እርሱን የመሰለ ውዳሴ በማለት በርሳቸው ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው ነው። ሁለተኛው: የረመዷንን ወር አግኝቶ ከዚያም አምልኮን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ምክንያት ከመማሩ በፊት ወሩ የተጠናቀቀበት ሰው ነው። ሶስተኛው: በእርጅና ወቅት ወላጆቹን አግኝቶ የነርሱን ሐቅ ባለመወጣቱና ሐቃቸውን በማጓደሉ ምክንያት ጀነት ለመግባቱ ሰበብ ያልሆኑለት ሰው ነው።فوائد الحديث
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ዋናው ፍሬ ሃሳብ እያንዳንዱ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት አካላት እድሉን ቢጠቀምበት ኖሮ ትልቅ መልካም የሆነን እድል የሚያገኝበት ነገር ነበረው። እድሉን በሚያመልጠው ልክ ማጓደሉ ግን ለክስረትና ለውርደት ዳረገው።"
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስም በተወሳ ቁጥር በርሳቸው ላይ ሶላት በማውረድ መነሳሳቱን እንረዳለን።
በረመዷን ወር ለአምልኮ በመዘጋጀትና በመታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ለወላጆች በጎ በማድረግና በመንከባከብ መታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በተለይ ባረጁ ወቅት የበለጠ መታገል ተገቢ ነው።
التصنيفات
ድንገተኛ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የሚባሉ ዚክሮች