በዱንያ ሐር የለበሰ ሰው በመጪው ዓለም አይለብሰውም።

በዱንያ ሐር የለበሰ ሰው በመጪው ዓለም አይለብሰውም።

ከዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በዱንያ ሐር የለበሰ ሰው በመጪው ዓለም አይለብሰውም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ሆኖ በዱንያ ሐር የለበሰ ሰው ተውበት እስካላደረገ ድረስ መቀጫ ሊሆነው ዘንድ በመጪው ዓለም እንደማይለብስ ገለፁ።

فوائد الحديث

ሐር በማለት የተፈለገው በተፈጥሮ ጥርት ያለውን ሐር እንጂ በፋብሪካ የሚሰራውን ሲንተቲክ ሐር ሐዲሡ አያካተውም።

በወንዶች ላይ ሐር መልበስ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

ሐርን የመልበስ ክልከላው መልበሱንም ሆነ ምንጣፍ ማድረጉን ያካትታል።

ለወንዶች ጎኑ ከሁለት ጣት እስከ አራት ጣት ያላለፈ የሆነ ለጥለት ወይም ለልብስ ገበር አድርገው ልብሳቸው ላይ የተወሰነ ሐር ቢጠቀሙ ይፈቀድላቸዋል።

التصنيفات

የአለባበስ ስነ-ስርዓት