የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ።

የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።

[ሐሰኑን ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት የሚያስገቡ ትልልቅ ምክንያቶች ሁለት መሆናቸውን ገለፁ። እነሱም: አላህን መፍራትና መልካም ስነምግባር ናቸው። አላህን መፍራት: በአንተና በአላህ ቅጣት መካከል መጠበቂያ ማድረግህ ነው። ይህም ትእዛዙን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ ነው። መልካም ስነምግባር ደሞ: ፊትን ፈታ በማድረግ ፣ መልካምን በመለገስና ከማወክ በመቆጠብ ነው። እሳት የሚያስገቡት ትልልቅ ምክንያቶች ደግሞ ሁለት ናቸው። እነሱም: ምላስና ብልት ናቸው። ከምላስ ወንጀሎች መካከል:- ውሸት፣ ሀሜት፣ ወሬ ማዋሰድና ሌሎችም ናቸው። ከብልት ወንጀሎች መካከል ደሞ:- ዝሙት፣ ግብረሰዶምና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።

فوائد الحديث

ጀነት መግባት ከአላህ ትእዛዝ ጋር የተገናኙ ምክንያቶች አሉት። ከነሱም መካከል:- አላህን መፍራትን ይመስል። ከሰዎች ጋር የተገናኙ ምክንያቶችም አሉት። ከነሱም መካከል:- መልካም ስነምግባርን ይመስል።

ምላስ እሳት ከመግቢያ ምክንያቶች መካከል ስለሆነ በባለቤቱ ላይ አደገኛ መሆኑ፤

የስሜት ተገዢ መሆንና ፀያፍ ወንጀሎችን መስራት በአብዛኛው እሳት የመግቢያ ምክንያቶች መካከል አንዱ ስለሆነ በሰው ላይ አደጋ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር, የጀነትና እሳት ባህሪዎች