إعدادات العرض
በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ…
በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።
ከኸውለህ ቢንት ሐኪም አስሱለሚየህ እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français اردو 中文 हिन्दी Bahasa Indonesia বাংলা Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ Русский ไทย Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Türkçe دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda नेपाली Српски Wolof Soomaali Moore Українська Български Tagalog Azərbaycan ქართული тоҷикӣ bm Oromoo Македонскиالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰው ልጅ አንድ ስፍራ ላይ በሚያርፍበት ጊዜ የሚፈራቸውን ሁሉ አስፈሪ ነገሮች የሚከላከልበትን ጠቃሚ መጠበቂያና መጠጊያ ለኡመታቸው እየጠቆሙ ነው። ይህም ጉዞም ላይ ይሁን ሊዝናናም ይሁን ወይም ከዛ ውጪ ባረፈበት ስፍራ ላይ ከሚገኝ ፍጡራን ሁሉ ክፋት በትሩፋቱ፣ በበረከቱና በጥቅሙ የተሟላ በሆነውና ከሁሉም ነውርና ጉድለት የፀዳ በሆነው የአላህ ቃል ከተጠበቀና ከተጠጋ በዛ ስፍራ እስካለ ድረስ ከሁሉም ጎጂ ነገሮች ደህንነቱ ይጠበቃል።فوائد الحديث
በአላህ መጠበቅ አምልኮ ነው። የተፈቀደ የሚሆነውም በአላህ ወይም በስሞቹና በባህሪያቶቹ ሲጠበቅ ነው።
ከአላህ ባህሪያቶች መካከል አንዱ በሆነው የአላህ ቃል መጠበቅ እንደሚፈቀድ እንረዳለን። ይህም በማንኛውም ፍጡር ከመጠበቅ ተቃራኒ ሲሆን ከአላህ ውጪ ካለ አካል ጥበቃን መሻት ሺርክ ነው።
የዚህ ዱዓእ ትሩፋትና በረከትን እንረዳለን።
በዚክሮች መመሸግ (መከላከል) ሰው ከክፋቶች እንዲጠበቅ አንዱ ሰበብ ነው።
በጋኔን ፣ በጠንቋይ፣ በአታላዮችና በሌሎችም ከአላህ ውጪ ባሉ አካላት ጥበቃ መፈለግ ውድቅ መደረጉ፤
ይህ ዱዓእ በሀገሩም ይሁን በጉዞ አንድ ስፍራ ላይ ላረፈ ሰው መደንገጉን እንረዳለን።
التصنيفات
ድንገተኛ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የሚባሉ ዚክሮች