አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!

አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!

ከአቡ ቀታዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳንድ ስርዓቶችን አብራሩ። ወንድ ልጅ በሚሸናበት ወቅት ብልቱን በቀኝ እጁ መያዙን ከለከሉ፤ ከፊት ለፊት ብልትም ይሁን ከኋላ ብልት የሚወጣን ነጃሳ በቀኝ እጅ ማስወገዱንም ከለከሉ፤ ምክንያቱም ቀኝ እጅ የተዘጋጀችው የተከበሩ ድርጊቶችን ለመፈፀም ነውና። ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው የሚጠጣበት እቃ ውስጥ መተንፈሱንም ከልክለዋል።

فوائد الحديث

በስነ-ስርዓት እና በንፅህና እስልምና ቀዳሚ መሆኑን መገለፁ።

ቆሻሻ ነገሮችን መራቅ እንደሚገባና የግድ መንካት ካለበትም በግራ መሆን እንዳለበት እንረዳለን።

የቀኝ እጅ ደረጃና ከግራ እጅ በላጭ መሆኑን መገለፁ።

እስላማዊ ድንጋጌ ምሉዕና አስተምህሮቶቹ ሁሉን አቀፍ መሆናቸውን እንረዳለን።

التصنيفات

የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት, የመፀዳጃ ቤት ስነ-ስርዓት