'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'

'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'"

[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች መካከል ኢማኑ የሞላው ስነምግባሩ ያማረ ሰው እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ለሰዎች ፊቱን ፈታ በማድረግ፣ መልካምን በመስጠት፣ ንግግርን በማሳመርና ሰዎችን ከማወክ በመቆጠብ ነው። ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ለምሳሌ ለሚስቱ፣ ለሴት ልጆቹ፣ ለእህቶቹና ለቅርብ ዘመዶቹ ምርጥ የሆኑ ናቸው። ምክንያቱም ሴቶች በመልካም ስነምግባር ሊኗኗራቸው ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የተገቡ ስለሆኑ ነው።

فوائد الحديث

የመልካም ስነምግባር ትሩፋትን እንረዳለን። እሱ ከኢማን የሚመደብ ነውና።

ተግባር ከኢማን የሚመደብ መሆኑን፤ ኢማን ይጨምራልም ይቀንሳልም።

ኢስላም ሴቶችን የሚያከብር እምነት መሆኑንና ለሴቶች መልካም በመስራት ላይ መበረታታቱንም እንረዳለን።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር, በትዳር ጥንዶች መካከል መኗኗር