ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።

ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የጠራውና ከፍ ያለው አላህ ከሰዎች ውስጥ ለእውነት እጅ መስጠትን የማይቀበል፣ እውነታውን በክርክሩ ለመመለስ የሚሞክር ወይም እውነትን ይዞ ቢከራከርም ነገር ግን ከሚዛናዊነት በሚያስወጣው መልኩ ክርክርን የሚያበዛና ያለ እውቀት የሚከራከርን ደረቅ ተከራካሪንና ክርክር የሚያበዛን እንደሚጠላ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

فوائد الحديث

ተበዳይ ሀቁን ሸሪዓዊ በሆነ መልኩ መክሰሱ የተወገዘ የሆነው የክርክር ይዘት ውስጥ አይገባም።

ክርክርና ንትርክ በሙስሊሞች መካከል ልዩነትንና ጀርባ መሰጣጠትን የሚየስከትሉ የምላስ ወለምታዎች ናቸው።

እውነትን ይዞና በጥሩ ዘይቤ ከሆነ ክርክር የተወደሰ ይሆናል። ውሸትን ለማፅናትና እውነትን ለመመለስ ከሆነ ወይም ያለማስረጃ ከሆነ ደግሞ የተወገዘ ክርክር ይሆናል።

التصنيفات

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት, ውግዝ ስነ-ምግባር