አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!

አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ መሆኑን ገለፁ። ይህም ሰጋጅ ከሰውነቱ የላቀና የተከበረው አካሉን ለአላህ በሱጁድ ለመዋደቅ፣ ለመዋረድና ለመተናነስ ሲል መሬት ላይ የሚደፋ በመሆኑ ነው። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሱጁድ ውስጥ ዱዓእ እንድናበዛም አዘዙን። በዚህም ንግግራዊም ድርጊታዊም መተናነስ ይሰባሰባሉ።

فوائد الحديث

አምልኮ ባሪያውን ወደ አላህ መቃረብን ትጨምርለታለች።

ሱጁድ ዱዓእ ተቀባይነት ከሚያገኝበት ስፍራዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ሱጁድ ውስጥ ዱዓእ ማብዛት እንደሚወደድ ተረድተናል።

التصنيفات

ዱዓእን ተቀባይነት የሚያስገኙና ተቀባይነት እንዳያገኝ የሚከለክሉ ምክንያቶች