إعدادات العرض
'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
ከአቢ በክረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?' እኛም 'እንዴታ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!' አልናቸው። እሳቸውም፦ 'በአላህ ማጋራት ፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል' አሉ። ደገፍ ብለው ከነበረበትም ተስተካክለው ተቀመጡና 'ንቁ! የውሸት ንግግርን (ተጠንቀቁ)።' አሉ። ምነው ዝም ባሉ እስክንል ድረስም ይህንን ከመደጋገም አልተወገዱም።"
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी বাংলা Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە ไทย دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Malagasy Italiano ಕನ್ನಡ Oromoo Română Wolof Soomaali Српски Moore Українська Български Tagalogالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለባልደረቦቻቸው እጅግ ትልቅ ስለሆነ ወንጀል ነገሯቸው። እነዚህን ሶስት ወንጀሎችንም ጠቀሱ፦ 1 - በአላህ ማጋራት፦ ይህም ከአምልኮ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አምልኮ ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ፣ ከአላህ ውጪ የሆነን አካል ከአላህ ጋር በተመላኪነቱ ወይ በጌትነቱ ወይም በስምና ባህሪያቱ እኩል ማድረግ ማለት ነው። 2 - የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፦ ይህም ወላጆች ላይ በንግግርም ይሁን በተግባር በማንኛውም መልኩ ማወክና ለነርሱ በጎ ማድረግን መተው ማለት ነው። 3 - ውሸት መናገር ነው። በውሸት መመስከርም እዚህ ውስጥ ይካተታል: ይህም ከተቀጠፈበት አካል ንብረቱን ለመውሰድ ወይም ክብሩ ላይ ወሰን ለማለፍ ወይም የመሳሰሉትን በመፈለግ የተቀጠፈና የተዋሸ ንግግር ሁሉ ማለት ነው። ከመደጋገማቸው የተነሳ ሶሐቦች ለነቢዩ ካላቸው እዝነትና የሳቸውን መረበሽ ጠልተው ምነው ዝም ባሉ ብለው እስኪመኙ ድረስ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የውሸትን ፀያፍነት እና ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረውን መጥፎ አሻራ ለማስገንዘብ ከሐሰተኛ ቃል ደጋግመው አስጠነቀቁ።فوائد الحديث
እጅግ ትልቁ ወንጀል በአላህ ላይ ማጋራት ነው። ምክንያቱም ሐዲሡ ላይ ከትላልቅ ወንጀሎች ሁሉ ግንባር ቀደምና ትልቁ አድርገው ጠቀሰውታልና። ይህንንም {አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም። ከዚህ ሌላ ያለውንም (ሀጢዐት) ለሚሻው ሰው ይምራል።} የሚለው የአላህ ንግግር ያጠናክረዋል።
ሐዲሡ ላይ የወላጆች ሐቅ ከአላህ ሐቅ ጋር በመቆራኘቱ የወላጆችን ሐቅ ታላቅነት እንረዳለን።
ወንጀሎች ወደ ትላልቅና ትናንሽ ይከፈላሉ። ትላልቅ የሚባሉት: ማንኛውም አለማዊ ቅጣት የተቀመጠለት ወንጀል ለምሳሌ :- ቅጣቱ በሸሪዓዊ መቅጫ ህግ ውስጥ ያለ (ሑዱድ)፣ መረጋገም ያለበት፤ ወይም እሳት መግባትን የመሰለ አኺራዊ ዛቻ የመጣበት ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለያዩ ደረጃዎች አላቸው። የክልከላ ደረጃውም ከፊሉ ከከፊሉ ይከብዳል። ትናንሽ ወንጀሎች የሚባሉት ደግሞ ከትላልቅ ወንጀሎች ውጪ ያሉት ናቸው።