አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!

አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!

ከዑመር ቢን አቢ ሰለማህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "በአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጎጆ ውስጥ የምኖር ህፃን ልጅ ነበርኩ። በማዕዱ ላይም እጄ ትሽከረከር ነበር። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኔ እንዲህ አሉኝ ' አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!' ከዚያን ጊዜ በኋላ ከዚህ የአበላል ስርአት አልተወገድኩም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ዑመር ቢን አቢ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት የሆነችው የኡሙ ሰለማህ ልጅ ነው። በሳቸው እነፃና እንክብካቤ ስር ነበር። በሚበላበት ወቅት ምግብ ለማንሳት እጁን በእቃው ዙሪያ ያዘዋውር ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶስት የአመጋገብ ስርአቶችን አስተማሩት: የመጀመሪያው: መብላት ሲጀመር "ቢስሚላሂ" ማለት ነው። ሁለተኛው: በቀኝ መብላት ነው። ሶስተኛው: ለርሱ ቅርብ በሆነ ምግብ በኩል መመገብ ነው።

فوائد الحديث

ከመብላትና መጠጣት ስርአቶች መካከል መጀመሪያ ቢስሚላህ ማለት አንዱ ነው።

ህፃናትን ስርአት ማስተማር እንደሚገባ በተለይ በሰውዬው ሀላፊነት ስር ያለን ልጅ ስርአት ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን።

ህፃናትን በማስተማርና ስርአት በማስያዙ ረገድ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እዝነትና ልበ ሰፊነትን እንረዳለን።

ከፊቱ ካለው መመገብ ከአመጋገብ ስርአቶች መካከል አንዱ ነው። የምግብ አይነቶቹ ብዙ የሆኑ ጊዜ ግን ከፊቱ ውጪ ካለ መውሰድም ይችላል።

ሶሐቦች ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስተማሯቸውን ስርአት አጥብቀው መያዛቸውን እንረዳለን። ይህንንም ነጥብ "ከዛን ጊዜ በኋላ ከዚህ የአበላል ስርአት አልተወገድኩም።" ከሚለው የዑመር ንግግር እንረዳለን።

التصنيفات

የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት